ደህና ፡ ነኝ (Dehna Negn) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን
(Kalkidan Tilahun)

Kalkidan Tilahun 5.jpg


(5)

ለእግዚአብሔር ፡ ቀላል ፡ ነው
(LeEgziabhier Qelal New)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 5:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃልኪዳን ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Kalkidan Tilahun)

ቀናቶቼ ፡ በከንቱ ፡ ዓመታቶቼ ፡ በችኮላ
እንዲሁ ፡ እንዳያልፉ ፡ ከዚህ ፡ በኋላ
ዘመኔን ፡ በሙሉ ፡ በፊቴ ፡ ያለውን
ያለ ፡ ፍሬ ፡ እንዳልሆን ፡ አስታጥቀኝ ፡ ኃይልን

አዝ፦ ደህና ፡ ደህና ፡ ነኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን (፭x)
ደህና ፡ ደህና ፡ ነኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን (፭x)

የሕይወቴን ፡ መጸሃፍ ፡ የጻፈው ፡ እግዚአብሔር
ደራሲው ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ተራኪዋ ፡ እኔ ፡ ነኝ (፪x)
የመጨረሻውን ፡ ምዕራፉን ፡ ሳነበው
ደህና ፡ ነሽ ፡ በሎኛል ፡ ደህና ፡ ነኝ ፡ እላለው (፪x)

አዝ፦ ደህና ፡ ደህና ፡ ነኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን (፭x)
ደህና ፡ ደህና ፡ ነኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን (፭x)

ሳለ ፡ መድሃኒያለም ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ
በቀኝም ፡ በግራም ፡ ሠላም ፡ አይደል ፡ ወይ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ እፎይ ፡ ብያለሁ
በአገሪቱ ፡ ላይ ፡ ተዘ. (1) . (፪x)

አዝ፦ ደህና ፡ ደህና ፡ ነኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን (፭x)
ደህና ፡ ደህና ፡ ነኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን (፭x)

እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ደህንነት ፡ ሆነልኝ
እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ እፎይታ ፡ ሆነልኝ
እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ጸጥታ ፡ ሆነልኝ
እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ሠላሜ ፡ ሆነልኝ

አዝ፦ ደህና ፡ ደህና ፡ ነኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን (፭x)
ደህና ፡ ደህና ፡ ነኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን (፭x)

ምሥጋና ፡ የሚገባው ፡ አምልኮ ፡ የሚገባው
ዝማሬ ፡ የሚገባው ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ነው (፪x)

አምልኮ ፡ የሚገባው ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ነው
መምስገን ፡ የሚገባው ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ነው
መወደድ ፡ የሚገባው ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ነው
መከብር ፡ የሚገባው ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ነው

እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ነው (፬x)