ቅጥር ፡ ሰርተህ (Qeter Sertehe) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን
(Kalkidan Tilahun)


(2)

ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው
(Gieta Eko New)

ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:50
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃልኪዳን ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Kalkidan Tilahun)

አዝ፦ ቅጥር ፡ ሰርተህ ፡ እኔን ፡ ከበህ
እንደ ፡ ዓይንህ ፡ ብሌን ፡ ተጠንቅቀህ
አቤት ፡ ጥበቃህ ፡ ጥበቃህ ፡ ያስደንቀኛል
ከክፉ ፡ ሁሉ ፡ ሁሉ ፡ አድነኸኛል (፪x)

እግዚአብሔር ፡ መሪ ፡ ነው ፡ ሁሌ ፡ ይመራኛል
ከረግረግ ፡ ከጭቃ ፡ እኔን ፡ ያወጣኛል
እግሬን ፡ በሰላሙ ፡ መንገድ ፡ የሚያቀና
የታመነ ፡ አምላክ ፡ ይድረሰው ፡ ምሥጋና

አዝ፦ ቅጥር ፡ ሰርተህ ፡ እኔን ፡ ከበህ
እንደ ፡ ዓይንህ ፡ ብሌን ፡ ተጠንቅቀህ
አቤት ፡ ጥበቃህ ፡ ጥበቃህ ፡ ያስደንቀኛል
ከክፉ ፡ ሁሉ ፡ ሁሉ ፡ አድነኸኛል

እግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ ወደ ፡ እውነት ፡ መርቶኛል
በትዕዛዛትህ ፡ እንድሄድ ፡ አድርጐኛል
የቅዱሳንህን ፡ እግር ፡ የምትጠብቅ
በክንፎችህ ፡ ጥላ ፡ እኔን ፡ የምትደብቅ

አዝ፦ ቅጥር ፡ ሰርተህ ፡ እኔን ፡ ከበህ
እንደ ፡ ዓይንህ ፡ ብሌን ፡ ተጠንቅቀህ
አቤት ፡ ጥበቃህ ፡ ጥበቃህ ፡ ያስደንቀኛል
ከክፉ ፡ ሁሉ ፡ ሁሉ ፡ አድነኸኛል

እርሱ ፡ የወደደው ፡ ተማምኖ ፡ ይኖራል
በትከሻው ፡ መሃል ፡ በክብርም ፡ ያድራል
እኔም ፡ ተወደድኩኝ ፡ ፍቅሩንም ፡ አየሁኝ
እግዚአብሔር ፡ ሳሳልኝ ፡ ተጠነቀቀልኝ

አዝ፦ ቅጥር ፡ ሰርተህ ፡ እኔን ፡ ከበህ
እንደ ፡ ዓይንህ ፡ ብሌን ፡ ተጠንቅቀህ
አቤት ፡ ጥበቃህ ፡ ጥበቃህ ፡ ያስደንቀኛል
ከክፉ ፡ ሁሉ ፡ ሁሉ ፡ አድነኸኛል (፬x)