From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የሚባርከኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የሚያድርግልኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የሚደርስልኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የሚመጣልኝ
እስኪቀደድ ፡ እስኪያፈስ ፡ መረቤ
የባረከኝ ፡ ተገኝቶ ፡ አጠገቤ
ባለቀለት ፡ ባበቃው ፡ ነገር ፡ ላይ
አደረገኝ ፡ ትንሳኤውን ፡ እንዳይ
ባከተመው ፡ በሞተው ፡ ነገር ፡ ላይ
አደረገኝ ፡ ትንሳኤውን ፡ እንዳይ
አዝ፦ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የሚባርከኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የሚያድርግልኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የሚደርስልኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የሚመጣልኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ አታዩትም ፡ ወይ
የባረከኝ ፡ ከአቅሜ ፡ በላይ
ልጐትተው ፡ አልቻልኩትምና
ጓደኞቼ ፡ እርዱኝ ፡ ተገኙና
ልሸከመው ፡ አልቻልኩትምና
ወዳጆቼ ፡ እርዱኝ ፡ ተገኙና
አዝ፦ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የሚያሳካልኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የሚያቃናልኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ያትረፈረፈኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ያረሰረሰኝ
እዛጋ ፡ ጣዪው ፡ መረቡን ፡ ሚለኝ
አሄ ፡ ብዬ ፡ መረቤን ፡ ጣልኩኝ
በበረከቱ ፡ አስደነገጠኝ
ይሄን ፡ ሁሉ ፡ መቼ ፡ ጠበኩኝ
በበረከቱ ፡ አስደነገጠኝ
ይሄን ፡ ሁሉ ፡ መቼ ፡ ጠበኩኝ
አዝ፦ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ክብር ፡ የሰጠኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ሞገስ ፡ የሰጠኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ውበት ፡ የሆነኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ . (1) .
በረከቱን ፡ መቼ ፡ ላከልኝ
እርሱ ፡ ራሱ ፡ ነው ፡ መጥቶ ፡ የሰጠኝ
በሰው ፡ መጠቀም ፡ አላስፈለገውም
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ቤቴ ፡ የገባው
በሰው ፡ መጠቀም ፡ አላስፈለገውም
ጌታዬ ፡ ነው ፡ ቤቴ ፡ የገባው
አዝ፦ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የሚያሸልለኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የሚያዘንጠኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ያንቀባረረኝ
ላመስግነው ፡ ለቀቅ ፡ አድርጉኝ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የሚያሸልለኝ
ጌታዬ ፡ ነው ፡ የሚያዘንጠኝ
ጌታዬ ፡ ነው ፡ ሕይወት ፡ የሰጠኝ
ላመስግነው ፡ ለቀቅ ፡ አድርጉኝ
|