ውብ ፡ ነህ (Web Neh) - ቃልኪዳን ጥላሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ቃልኪዳን ጥላሁን
(Kalkidan Tilahun)

Kalkidan Tilahun 7.jpg


(7)

አልበም
(Eyulign)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2021)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 5:07
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃልኪዳን ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Kalkidan Tilahun)

አንተኮ ውብ ነህ (4)
እየሱስ ውብ ነህ (4)

አንተ የዋህ ነህ በልብህ ትሁት
ቀንበርህ ልዝብ ነው ሸክምህ ቀሊል
ካንተ ጋር መኖር ምን ያቅተኛል
ህይወቴን ቀላል አርገህልኛል

የዳዊት ስርና ዘር
የሚያበራ የንጋት ኮከብ
የእግዚአብሔር ልጅ የሆነውን
እየሱስን አመልካለሁኝ
አመልካለሁኝ (3)
አመልካለሁ
አመልካለሁኝ (2)

የከበረ የተፈተነውን
መሰረቱ የፀናውን
የማእዘን እራስ የሆነውን
እየሱስን አመልካለሁኝ
አመልካለሁኝ (3)
አመልካለሁ
አመልካለሁኝ (2)

ድንቅ መካር ሀያል አምላክ
የሰላምም አለቃ
የዘላለም አባት የሆነውን
እየሱስን አመልካለሁኝ
አመልካለሁኝ (3)
አመልካለሁ
አመልካለሁኝ (2)