ማነው (Manew) - ቃልኪዳን ጥላሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ቃልኪዳን ጥላሁን
(Kalkidan Tilahun)

Kalkidan Tilahun 7.jpg


(7)

አልበም
(Eyulegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2021)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:32
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃልኪዳን ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Kalkidan Tilahun)

እስትንፋስ ያላቸው ፍጥረታት በሙሉ
 እግዚአብሔር ትልቅ ነው ትልቅ ነው ይላሉ
 አንዳንዱ ፈልጎ አንዳንዱ በግድ
አያስደንቅ ወይ ለእግዚአብሔር ሲሰግድን

ማነው እንዳንተ ማነው?4x
እንዳንተ ማነው?4x

አህዛብ ደንግጡ ምድርን ተፍራው
ፈላጭ ቆራጩ እሱ ብቻ ነው
ታፍሮና ተከብሮት በዙፋኑ ያለው
 ከእግዚአብሔር በስተቀር የትኛው አምላክ ነው?

ማነው እንዳንተ ማነው?4x
እንዳንተ ማነው?4x

የእድሜ ባለ ጸጋ ሁሌ አንፀባራቂ
ለሰማይ ለምድሩ ለፍጥረቱ በቂ
ከዘላለም በፊት ከጥንት የነበረው
እግዚአብሔርን በዕድሜ የሚበልጠው ማነው

ማነው እንዳንተ ማነው?4x
እንዳንተ ማነው?4x

የነገስታትን ወገብ የሚፈታ የሚፈታ ያኔ ጌታ
ብቻውን ብዙ ገጥሞ የሚረዳ የኔ ጌታ
ቃላቶች ተጨምቀው አንድ ቃል ቢሆኑም
ያንተን ትልቅነት ሊገልፁት አይችሉም

ማነው የላቀ የደመቀ በዓለም የታወቀ
ማነው ያወቀ የረቀቀ ሁሌ የተደነቀ
ማነው የጸና ያልወደቀ ሁሌ እንደደመቀ
በትረ መንግስቱን ያለቀቀ ዘመኑ ያላለቀ

እናገራለሁኝ እግዚአብሔር ነው ብዬ
 እመሰክራለሁ እግዚአብሔር ነው ብዬ
በግምት አይደለም የምናገረው
ሁሉን ቻይነቱን ስለማውቀው ነው
በመላ እኮ አይደለም የምናገረው
ሁሉን ቻይነቱን ስለማውቀው ነው

ማነው እንዳንተ ማነው?4x
እንዳንተ ማነው?4x