ገና ፡ ሳይከፈል ፡ ባህሩ (Gena Saykefel Bahiru) - ቃልኪዳን ጥላሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ቃልኪዳን ጥላሁን
(Kalkidan Tilahun)

Kalkidan Tilahun 7.jpg


(7)

7
(7)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2021)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃልኪዳን ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Kalkidan Tilahun)

ሁኔታ መጣና ጠየቀኝ
ዛሬም ታመልኪያለሽ ወይ አለኝ
ነገሩ መጣና ጠየቀኝ
ዛሬም ታመልኪያለሽ ወይ አለኝ
ከፍታው መጣና ጠየቀኝ
ዛሬም ታመልኪያለሽ ወይ አለኝ

አዎ አመልካለው ከፍ አደርገዋለሁ
አዎ አመልካለው እባርከዋለሁ
አዎ አመልካለው ከፍ አደርገዋለሁ
ከፍ አደርገዋለሁ

ገና ሳይከፈል ባህሩ
ሳይሳካ ነገሩ (2)
እስቲ ላንሳ ከበሮውን
ላመስግነው እግዚአብሔርን (2)
ተመስገን ተመስገንልኝ
ተመስገንልኝ(4)

በባዶ እንዳመሰግንህ
አምላኬ /አንተ እኮ/ እድል ሰጥተኸኛል
ላሳይህ እንዴት እንደማምንህ
በባዶ እያመሰገንኩኝ

ተመስገን ተመስገንልኝ
ተመስገንልኝ

እኔ ዝም ብዬ አልፈዝም
ነገር ነገሩን አላይም
ገነጣጥዬ እወጣለሁ
አምላኬን በጬኸት አመልከዋለሁ

ተመስገን ተመስገንልኝ
ተመስገንልኝ

ዝም አልልም አመሰግናለሁ
ለጌታዬ ክብርን እሰጣለሁ
የጠላቴን ንዝነዛ እምቢ ብዬ
ላመስግነው ላክብረው ጌታዬ

አመሰግናለሁ

ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ
ክፉ ሁሉ ለጥሩ እንዲለወጥ
ይህንንም ጨምሬ አውቃለሁ
ስለዚህም አመሰግናለሁ

አመሰግናለሁ