From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን (Kalkidan Tilahun)
|
|
፪ (2)
|
ጨለማዬን ጌታ እያበራ (chelemayen geta eyabera)
|
ቁጥር (Track):
|
፪ (2)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የቃልኪዳን ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች (Albums by Kalkidan Tilahun)
|
|
ምስጋና ነው በአፌ የሞላዉ
ተትረፍርፏል ለአምላኬ ላፍስሰው 2X
በከፍታዎች ላይ ለሚያቆመኝ ጌታ
እስኪ ላመስግነው ልዘምር በእልልታ
ወንጭፌን ሞልቶታል ክብርና ምስጋና
የጠላቴን አንገት ረግጫለሁና
ምስጋና ነው በአፌ የሞላዉ
ተትረፍርፏል ለአምላኬ ላፍስሰው 2X
ጌታዬን ታምኜ ጎልያድን ገጠምኩት
በጭፍራዎቹ ፊት ጥዬ አዋረድኩት
የለበሰው ብረት ለካ ከንቱ ነበር
በአንዲት ጠጠር ብቻ ወድቆ የሚሰበር
ምስጋና ነው በአፌ የሞላዉ
ተትረፍርፏል ለአምላኬ ላፍስሰው 2X
የእስራኤል ተዋጊ ቅዱስ እግዚአብሔር
በበረዶ ድንጋይ ጠላት የሚያባርር
የእኔም ጌታ እርሱ ነው የሚሳነው የለም
ዛሬም ለጠላቴ ወደኋላ አላለም
ምስጋና ነው በአፌ የሞላዉ
ተትረፍርፏል ለአምላኬ ላፍስሰው 2X
የጠላቴን መንደር ለሚያወርሰኝ ጌታ
እስኪ ላመስግነው ልዘምር በደስታ
አትፍሪ እያለ ለሚያበረታኝ
ለሚያከብረኝ ለእሱ ምስጋና አለኝ
ምስጋና ነው በአፌ የሞላዉ
ተትረፍርፏል ለአምላኬ ላፍስሰው X
|