Kalkidan Tilahun/Chelemayen Geta Eyabera/Misgana Tewedalehena

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ቃልኪዳን ጥላሁን ርዕስ ምስጋና ትወዳለህና

አምላክና መድሐኒት ለሆንከው ከእኔ በቀር አዳኝ የለም ላልከው 2X ለአንተ ለእግዚአብሔር ክብርን ሰጣለሁ 2X ለአንተ ለአምላኬ ክብርን ሰጣለሁ 2X

ምስጋና ትወዳለህና (አምላኬ አመሰግናለሁ)2X አምልኮ ትወዳለህና (አምላኬ እኔ አመልክሀለው)2X ሞገስን ትወዳለህና (ጌታዬ አሞግስሀለው)2X መከበር ትወዳለህና (አምላኬ እኔ አከብርሀለው)2X ለአንተ ለእግዚአብሔር ክብርን ሰጣለሁ 2X ለአንተ ለአምላኬ ክብርን ሰጣለሁ 2X

አትገመትም በጥቂት ነገር አንተ ትልቅ ነህ እንዴት ልናገር አፌን በአንተ ላይ አላላክክም አንተ ፃድቅ ነህ አትሳሳትም2X

ምስጋና ትወዳለህና (አምላኬ አመሰግናለሁ)2X ሙገሳን ትወዳለህና (ጌታዬ አሞግስሀለው) 2X መወደድ ትወዳለህና (ጌታዬ እኔ እወድሃለሁ)2X መወደስ ትወዳለህና (ጌታዬ እወድስሀለው)2X ለአንተ ለእግዚአብሔር ክብርን ሰጣለሁ 2X ለአንተ ለአምላኬ ክብርን ሰጣለሁ 2X

አምላክና መድሐኒት ለሆንከው ከእኔ በቀር አዳኝ የለም ላልከው 2X ለአንተ ለእግዚአብሔር ክብርን ሰጣለሁ 2X ለአንተ ለአምላኬ ክብርን ሰጣለሁ 2X

እኔ ዝቅ ብዬ አንተ ከፋ በል ክብር ምስጋናን ከእኔ ተቀበል አንተ ብቻህን ሁሉን ሰርተሀል ሁሉን ስትሰራ ማን አማክሮሀል

ምስጋና ትወዳለህና (አምላኬ አመሰግናለሁ)2X አምልኮ ትወዳለህና (አምላኬ እኔ አመልክሀለው)2X መከበር ትወዳለህና አምላኬ (እኔ አከብርሀለው)2X መሞገስ ትወዳለህና (ጌታዬ አሞግስሀለው)2X ለአንተ ለእግዚአብሔር ክብርን ሰጣለሁ 2X ለአንተ ለአምላኬ ክብርን ሰጣለሁ 2X

ከግብፅ ምድር ከብረት እቶን እኔን አወጣህ ርስትህ እንድሆን ሳላጉረመርም አመልክሀለው እንዳንተ ያለ የት አገኛለው 2X

አምላክና መድሐኒት ለሆንከው ከእኔ በቀር አዳኝ የለም ላልከው 2X ለአንተ ለእግዚአብሔር ክብርን ሰጣለሁ 2X ለአንተ ለአምላኬ ክብርን ሰጣለሁ 2X

እልልታን ትወዳለህና አምላኬ እልል ላለሁ አምላኬ እልልላለሁኝ ዝማሬ ትወዳለህና አምላኬ አዜምልሀለው አምላኬ አዜምልሀለው እዘምራለው 3X