ምስጋና ነው ባፌ የሞላው (Misgana New Bafe Yemolaw) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ምስጋና ነው ባፌ የሞላው
ተትረፍርፏል ላምላኬ ላፍሰው

በከፍታዋች ላይ ለሚያቆመኝ ጌታ
እስቲ ላመስግነው ልዘምር በእልልታ
ወንጭፌን ሞልቶታል ክብርና ምስጋና
የጠላቴን አንገት ረግጫለሁና

ምስጋና ነው ባፌ የሞላው
ተትረፍርፏል ላምላኬ ላፍሰው

ጌታዬን ታምኜ ጎልያድን ገጠምኩት
በጭፍራዎቹ ፊት ጥዬ አዋረድኩት
የለበሰው ብረት ለካ ከንቱ ነበር
ባንዲት ጠጠር ብቻ ወድቆ የሚሰበር

ምስጋና ነው ባፌ የሞላው
ተትረፍርፏል ላምላኬ ላፍሰው

የእስራኤል ተዋጊ ቅዱስ እግዚአብሔር
በበረዶ ድንጋይ ጠላቴን ሚያባርር
የኔም ጌታ እርሱ ነው የሚሳነው የለም
ዛሬም ለጠላቴ ወደኋላ አላለም

ምስጋና ነው ባፌ የሞላው
ተትረፍርፏል ላምላኬ ላፍሰው

የጠላቴን መንደር ለሚያወርሰኝ ጌታ
እስቲ ላመስግነው ልዘምር በደስታ
አትፍሪ እያለ ለሚያበረታኝ
ለሚያከብረኝ ለእርሱ ምስጋና አለኝ

ምስጋና ነው ባፌ የሞላው
ተትረፍርፏል ላምላኬ ላፍሰው