ምን እሻለሁ (Men Eshalehu) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን
(Kalkidan Tilahun)

Lyrics.jpg


(Volume)

አልበም
(Chelemayen Geta Eyabera)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፹ ፱ (1997)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃልኪዳን ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Kalkidan Tilahun)

ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ጌታዬ
አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ
ምን ፡ እሻለሁ ፡ ባይኖችህ ፡ ታይቻለሁ
ምን ፡ እሻለሁ ፡ በጆሮህ ፡ ተሰምቻለሁ
ምን ፡ እሻለሁ ፡ በእጆችህ ፡ ተይዣለሁ
ምን ፡ እሻለሁ ፡ በፊትህ ፡ ከብሬአለሁ

የእግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ
ደስ ፡ የሚል ፡ መንፈስ ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ
የሚያረሰርስ ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ

ደስታን ፡ ይሞላል ፡ ይባርካል
ሕዝቡን ፡ በእጆቹ ፡ ይዳስሳል
የተራበች ፡ ነፍስ ፡ ትጠግባለች ፡
ያዘነችውም ፡ ትጽናናለች

አዝ፦ የእግዚአብሔር ፡ መንፈስ ...

ተራራው ፡ ሜዳ ፡ የሆነው
በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በብርታት ፡ ነው
ቁርጭምጭሚትን ፡ የምታጸና ፡
የሕዝብህ ፡ ጉልበት ፡ አንተ ፡ ነህና

አዝ፦የእግዚአብሔር ፡ መንፈስ ...

ሰላምህ ፡ ፈሰሰ ፡ እንደ ፡ ጅረት
አርነት ፡ በዛ ፡ ባለህበት
ደንዳናው ፡ ሁሉ ፡ ፈራረሰ
በመንፈስህ ፡ ዘይት ፡ ረሰረሰ

አዝ፦የእግዚአብሔር ፡ መንፈስ ...