Kalkidan Tilahun/Chelemayen Geta Eyabera/Kitir Sertehe

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ


ቅጥር ሰርተህ እኔን ከበህ እንደ ዓይንህ ብሌን ተጠንቅቀህ አቤት ጥበቃህ ጥበቃህ ያስደንቀኛል ከክፉ ሁሉ ሁሉ አድነኸኛል (፪x)

እግዚአብሔር መሪ ነው ሁሌ ይመራኛል ከረግረግ ከጭቃ እኔን ያወጣኛል እግሬን በሰላሙ መንገድ የሚያቀና የታመነ አምላክ ይድረሰው ምሥጋና ቅጥር ሰርተህ... እግዚአብሔር መንፈስ ወደ እውነት መርቶኛል በትዕዛዛትህ እንድሄድ አድርጐኛል የቅዱሳንህን እግር የምትጠብቅ በክንፎችህ ጥላ እኔን የምትደብቅ

ቅጥር ሰርተህ...

እርሱ የወደደው ተማምኖ ይኖራል በትከሻው መሃል በክብርም ያድራል እኔም ተወደድኩኝ ፍቅሩንም አየሁኝ እግዚአብሔር ሳሳልኝ ተጠነቀቀልኝ

ቅጥር ሰርተህ