Kalkidan Tilahun/Chelemayen Geta Eyabera/Betalaq Girma Bezufanu Lalew

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ቃልኪዳን ጥላሁን ርዕስ በታላቅ ግርማ በዙፋኑ ላለው ጨለማየን ጌታ እያበራ

በታላቅ ግርማ በዙፋኑ ላለው የምስጋና ዘውድ በራሱ ለጫነው እዘምራለሁ (4x)

እኔ አፌን አልከፍትም ለአለም ክብር እዘምራለሁኝ ለእግዚአብሔር (2) እቀኝለታለሁ በአዲስ አዲስ ዜማ የምስጋናየ ድምፅ በአርያም ይሰማ (2x)

በታላቅ ግርማ በዙፋኑ ላለው የምስጋና ዘውድ በራሱ ለጫነው እዘምራለሁ (4x)

በጠዋት በማታ በቀን በሌሊቱ እሰዋለታለሁ ምስጋናን በፊቱ (2x) እያደነኩና እየተደነኩ እግዚአብሔር አምላኬን አመልከዋለሁ (2x)

በታላቅ ግርማ በዙፋኑ ላለው የምስጋና ዘውድ በራሱ ለጫነው እዘምራለሁ (4x)

በታላቅ ጉባኤ ሰውም በበዛበት ለእስራኤል ቅዱስ ቅኔን ልቀኝለት (2x) ከንፈሮቼም እጅግ እጅግ ደስ አላቸው ዝማሬ ሲያቀርቡ ለፈጣሪያቸው (2x)

በታላቅ ግርማ በዙፋኑ ላለው የምስጋና ዘውድ በራሱ ለጫነው እዘምራለሁ (4x)