አንተ ትበቃኛለህ (Ante Tebekanyaleh) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን
(Kalkidan Tilahun)

Lyrics.jpg


(Volume)

አልበም
(ጨለማዬን ጌታ እያበራ)

ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃልኪዳን ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Kalkidan Tilahun)

አንተ ትበቃኛለህ የእኔ ጌታ”
በዘማሪት ቃልኪዳን ጥላሁን

እንታነጽበት ዘንድ አቅራቢ
ወንድም ሶካ



አንተ ትበቃኛለህ የእኔ ጌታ
ሌላ ምንስ ያሻኛል?
አንተ ትበቃኛለህ ጌታዬ ሆይ
ሌላ ምንስ ያሻኛል?

[እግዚአብሔር አለልኝ
አለልኝ እኔ] 4

በእረፍት ውኃ ዘንድ ሁሌ የሚመራኝ
በለመለመው መስክ እረፍት የሚሰጠኝ
ነፍሴን የሚመልስ እኔን የሚረዳኝ
የዘለዓለም አምላክ እግዚአብሔር አለልኝ

አንተ ትበቃኛለህ……

እግዚአብሔር አለልኝ
አለልኝ እኔ /2
ጌታዬ አለልኝ እኔ
አለልኝ እኔ
የሱሴ አለልኝ እኔ
አለልኝ እኔ

ሳዝን የሚያጽናናኝ አይዞሽ የሚለኝ
ከጎኔ እየሆነ የሚያበረታኝ
ፍቅሩ የማይለወጥ ሁሌ ያው የሆነው
ከራሱ አስበልጦ ሰውን የሚወደው

እግዚአብሔር አለልኝ
አለልኝ እኔ /2
ጌታዬ አለልኝ እኔ
አለልኝ እኔ
የሱሴ አለልኝ እኔ
አለልኝ እኔ

አንተ ትበቃኛለህ……

እግዚአብሔር አለልኝ …
ጌታዬ አለልኝ እኔ
አለልኝ እኔ
የሱሴ አለልኝ እኔ
አለልኝ እኔ

ለነፍሴ ጥያቄ ጥሩ መልስ የሆነው
ከጎናችን ሆኖ ልቤን ያሳረፈው
እግዚአብሔር ካለልኝ ምን ያስፈልገኛል?
የእርሱ ሕልውና ለእኔ ይበቃኛል

አንተ ትበቃኛለህ……

እግዚአብሔር አለልኝ …

ጌታዬ አለልኝ እኔ
አለልኝ እኔ
የሱሴ አለልኝ እኔ
አለልኝ እኔ

እግዚአብሔር አለልኝ …

ጌታዬ አለልኝ እኔ
አለልኝ እኔ
የሱሴ አለልኝ እኔ
አለልኝ እኔ