Kalkidan Tilahun/Beyet Hager New Egziabhier/Yalemehereteh

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ


ዘማሪ ቃልኪዳን ጥላሁን ሌላ ሥም ሊሊ ርዕስ ያለምህረትህ ምን አለኝ

ያለ ይቅርታህ ምን አለኝ ምን አለኝ ጌታዬ ሆይ (፬x) ያለምህረትህ ምን አለኝ ያለ ይቅርታህ ምን አለኝ ምን አለኝ ጌታዬ ሆይ(፮x)

የምህረት ደጆችህ ተከፍተውልኛል እጅህም ለእኔ ተዘርግቶልኛል (፪x) እመጣለሁ ወደ አንተ እገባለሁ የእኔ ጌታ እገባለሁ እገባለሁ የእኔ ጌታ እመጣለሁ ወደ አንተ እመጣለሁ የእኔ ጌታ እመጣለሁ እመጣለሁ

ያለምህረትህ ምን አለኝ ያለ ይቅርታህ ምን አለኝ ምን አለኝ ጌታዬ ሆይ (፬x)

የእኔ መታመኛ ምህረትህ ብቻ ነው ድፍረት የሚሰጠኝ የፍቅር ፊትህ ነው (፪x) እመጣለሁ ወደ አንተ እመጣለሁ የእኔ ጌታ እገባለሁ እገባለሁ ወደ አንተ እመጣለሁ የእኔ ጌታ እመጣለሁ ወደ አንተ እመጣለሁ እመጣለሁ የእኔ ጌታ

ተባረክ ጌታ ተባረክ ተባረክ ኢየሱስ ተባረክ ተባረክ ጌታ ተባረክ ተባረክ ኢየሱስ ተባረክ (፪x)

ኢየሱስ መባና መሰዋእት ኢየሱስ የመዓዛ ሽታ ኢየሱስ አድርጐ እራሱን ኢየሱስ የሰጠኝ ጌታ ኢየሱስ እኔ አመልከዋለሁ ኢየሱስ ቀንም ሆነ ማታ

የርህራሄ አባት የመጽናናት ሁሉ አምላክ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ የርህራሄ አባት የመጽናናት ሁሉ አምላክ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ

ተባረክ ጌታ ተባረክ ተባረክ ኢየሱስ ተባረክ (፭x)