From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ትልቅ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ አእምሮ ፡ ሊሸከመው ፡ ከሚችለው ፡ በላይ (፬x)
ኦ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ትልቅ (፫x)
ኦ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ትልቅ (፫x)
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ ትልቅ ፡ ነው (፪x)
ትልቅነትህን ፡ ያላየ ፡ ማነው (፫x)
ትልቅነትህን ፡ ያልሰማ ፡ ማነው (፫x)
እኔስ ፡ አይቻለሁ ፡ ትልቅነትህን
ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ አንተ ፡ መብለጥህን
እኔ ፡ እንኳን ፡ አይቻለሁ ፡ ትልቅነትህን
ከነገሮች ፡ በላይ ፡ አንተ ፡ መብለጥህን
እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ትልቅነትህን
ከሁኔታዎች ፡ አንተ ፡ መብለጥህን
አንተ ፡ እኮ ፡ እጅግ ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፪x)
አምላኬ ፡ እጅግ ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፪x)
በሠማዩ ፡ ስፍራ ፡ በክብር ፡ ላለኸው
ምሥጋናዬ ፡ ይኸው ፣ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው
በሠማዩ ፡ ስፍራ ፡ በክብር ፡ ላለኸው
አምልኮዬ ፡ ይኸው ፣ አምልኮዬ ፡ ይኸው
አይመረመርም ፡ ከፍ ፡ ማለቱ ፡ የእርሱ ፡ ልቀቱ ፡ ጌታዬ
አይመረመርም ፡ ተወዳዳሪ ፡ አቻ ፡ ማጣቱ ፡ ጌታዬ
አይመረመርም ፡ ውበት ፡ ቁንጅና ፡ ድምቀት ፡ ማማሩ ፡ ጌታይ
አይመረመርም ፡ ግርማ ፡ ሞገሱ ፡ አስፈሪነቱ ፡ ጌታዬ
ሃ ፡ ሃ ፡ ሃሌሉያ (፬x)
አይመረመርም ፡ የርህራሄው ፡ የምህረቱ ፡ ብዛቱ
አይመረመርም ፡ ቸርነቱ ፡ ይቅር ፡ ማለቱ ፡ ጌታዬ
አይመረመርም ፡ ፍቅሩ ፡ ጥልቀቱ ፡ ወርዱ ፡ ስፋቱ
አይመረመርም ፡ ሰውን ፡ መውደዱ ፡ አዳኝነቱ ፡ ጌታዬ
ሃ ፡ ሃ ፡ ሃሌሉያ (፬x)
ትልቅ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ አእምሮ ፡ ሊሸከመው ፡ ከሚችለው ፡ በላይ (፬x)
ኦ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ትልቅ (፫x)
ኦ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ትልቅ (፫x)
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ ትልቅ ፡ ነው (፪x)
ትልቅነትህን ፡ ያላየ ፡ አለ ፡ ወይ? (፫x)
ትልቅነትህን ፡ ያልሰማ ፡ አለ ፡ ወይ? (፫x)
እኔኮ ፡ አይቻለሁ ፡ ትልቅነትህን
ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ አንተ ፡ መብለጥህን
እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ትልቅነትህን
ከሁኔታዎች ፡ አንተ ፡ መብለጥህን
አንተ ፡ እኮ ፡ እጅግ ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፪x)
አምላኬ ፡ እጅግ ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፪x)
የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የምድር ፡ ፈጣሪ
በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነዋሪ
የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ ነፍሴ ፡ ታከብርሃለች (፪x)
የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ ነፍሴ ፡ ታከብርሃለች (፪x)
የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ ነፍሴ ፡ ታከብርሃለች (፪x)
ነፍሴ ፡ ታከብርሃለች (፬x)
|