ቅዱስ ፡ ቅዱስ (Qedus Qedus) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን
(Kalkidan Tilahun)

Kalkidan Tilahun 6.jpg


(6)

በየት ፡ ሃገር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
(Beyet Hager New Egziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 8:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃልኪዳን ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Kalkidan Tilahun)

ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ያለና ፡ የነበረ ፡ የሚመጣ
ሁሉን ፡ የሚገዛ (፪x)
እያሉ ፡ ቀንና ፡ ሌሊት ፡ አይርፉም (፬x)

የሠማይ ፡ ሰራዊት ፡ ያገለግሉሃል
በቀን ፡ በሌሊቱ ፡ ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ይሉሃል (፪x)
እኔም፡ በአቅሜ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ
ሰው ፡ ላረከኝ ፡ ጌታ ፡ ምሥጋናን ፡ እሰዋለሁ (፪x)

እያሉ ፡ ቀንና ፡ ሌሊት ፡ አይርፉም (፬x)

መሆን ፡ እወዳለሁ ፡ ሁልጊዜ ፡ በፊትህ
ተመስገን ፡ እንድልህ ፡ እንዳገለግልህ (፪x)
መሆን ፡ እወዳለሁ ፡ ሁልጊዜ ፡ በፊትህ
ተባረክ ፡ እንድልህ ፡ እንዳገለግልህ (፪x)
መሆን ፡ እወዳለሁ ፡ ሁልጊዜ ፡ በፊትህ
ከፍ ፡ በል ፡ እንድልህ ፡ እንዳገለግልህ (፬x)

ሃሌሉያ ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ (፬x)
ሃሌሉያ ፡ ሃሌ (፬x)

አቤቱ ፡ አምላኬ ፡ ተወደስ
በልጆችህ ፡ ተቀደስ
ምሥጋናችን ፡ ለእአምላካችን
ያማረ ፡ ነው ፡ የሁላችን

ክብር ፡ ክብር ፡ ክብር ፡ ሃሌሉያ
ክብር ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ሃሌሉያ
ሞገስ ፡ ሞገስ ፡ የሌለህ ፡ እኩያ
የሌለህ ፡ እኩያ ፡ የሌለህ ፡ እኩያ (፪x)

ሃሌሉያ (፫x) ፡ (ሃሌሉያ)
ሃሌሉያ (፪x) ፡ ሃሌሉያ
ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌሉያ

ሃሌሉያ ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ (፬x)
ሃሌሉያ ፡ ሃሌ (፬x)

በፍቅርህ ፡ ዘይት ፡ ነፍሴን ፡ አረስርሰሃል (፪x)
ተባረክልኝ ፡ ጌታዬ
በምህረትህ ፡ ዘይት ፡ ነፍሴን ፡ አረስርሰሃል (፪x)
ተባረክልኝ ፡ ጌታዬ

ሥምህ ፡ እንደሚፈስ ፡ ዘይት ፡ ነው
ደናግሎች ፡ አይተው ፡ ወደዱህ (፭x)
እኛም ፡ አየንህ ፡ ጌታ ፡ ወደድንህ
መልካም ፡ የመዓዛ ፡ ሽታ ፡ አንተ ፡ አለህ
እኔም ፡ አይቼ ፡ ይህን ፡ ውዴ ፡ ወደድኩህ
መልካም ፡ የመዓዛ ፡ ሽታ ፡ አንተ ፡ አለህ (፫x)

በፍቅርህ ፡ ዘይት ፡ ነፍሴን ፡ አረስርሰሃል (፪x)
ተባረክልኝ ፡ ጌታዬ
በምህረትህ ፡ ዘይት ፡ ነፍሴን ፡ አረስርሰሃል (፪x)
ተባረክልኝ ፡ ጌታዬ

በማለዳ ፡ ምሥጋና ፡ በሌሊትም ፡ ዝማሬ
ሁኔታ ፡ አለወጥህ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እስከዛሬ
በማለዳ ፡ ምሥጋና ፡ በሌሊትም ፡ ዝማሬ
ነገሮች ፡ አለወጡህ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እስከዛሬ

አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ (፬x)
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ (፬x)
ስደክም ፡ ጉልበቴ ፡ ስበረታ ፡ ክብሬ
አንተ ፡ አልተለወጥክም ፡ ኢሄው ፡ እስከዛሬ
ቀናቶች ፡ ሲያልፉ ፡ አመታት ፡ ሲሆኑ
የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ አለ ፡ በዙፋኑ

በማለዳ ፡ ምሥጋና ፡ በሌሊትም ፡ ዝማሬ
ሁኔታ ፡ አለወጥህ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እስከዛሬ
በማለዳ ፡ ምሥጋና ፡ በሌሊትም ፡ ዝማሬ
ነገሮች ፡ አለወጡህ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እስከዛሬ
አንተ ፡ ነህ ፡ እስከዛሬ (፪x)