Kalkidan Tilahun/Beyet Hager New Egziabhier/Ejeg Yemimer

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ቃልኪዳን ጥላሁን ሌላ ሥም ሊሊ ርዕስ እጅግ የሚምር አልበም በየት ሃገር ነው እግዚአብሔር

ጻድቅ ነህ ጌታ ስራህ ትክክል የማታደላ የማትበድል ለታላቅነትህ ፍጻሜ የለው አቤት ጌታም ሆይ ስራህ ድንቅ ነው

ምላሴ ጽድቅህን ሁልጊዜ ምሥጋናህን ይናገራል (፫x) ምላሴ ጽድቅህን ሁልጊዜ ምሥጋናህን ይናገራል (፫x)

ደግሜ ደጋግሜ እባርክሃለሁ ምሥጋና ዘወትር ዘወትር በአፌ ነው ማለዳ በምሥጋና አፌን እከፍታለሁ ከአንደበቴ ፍሬ ለአንተው እነግራለሁ

ምላሴ ጽድቅህን ሁልጊዜ ምሥጋናህን ይናገራል (፫x) ምላሴ ጽድቅህን ሁልጊዜ ምሥጋናህን ይናገራል (፫x)

አዝ እጅግ የሚምር የሚራራ አምላክ ነውና የእኔ ጌታ ይድረሰው ምሥጋና የእኔ ጌታ ይድረሰው ምሥጋና (፪x)

እንኳንስ ምረሄኝ ቀርቶልኝ አበሳ (፪x) እኔስ ምሥጋናዬን ሁልጊዜው አልረሳ (፪x) ምህረትህ በእኔ ላይ ጠንክራለችና (፪x) ኃይሌ ታድሶልኝ ቆምኩኝ እንደገና (፪x)

አዝ እጅግ የሚምር የሚራራ አምላክ ነውና የእኔ ጌታ ይድረሰው ምሥጋና የእኔ ጌታ ይድረሰው ምሥጋና የእኔ ጌታ ይድረሰው ምሥጋና (፬x)

ማዳኑን አስታውቆ ጽድቁንም ገለጠ (፪x) ከእኛ መተላለፍ ምህረቱ በለጠ (፪x) በሞገሱ ጋሻ እየከለለን (፪x) ከአዳነን በኋላ ምህረቱ ያዘን (፪x)

አንድ ላይ ተስማሙ እውነትና ምህረት (፪x) መግባትም ተቻለን እግዚአብሔር ካለበት (፪x) ጻድቅ ፈራጅ ሲሆን እንከን የሌለበት (፪x) አልፈረደብኝም ምህረቱ አይሎበት (፪x)

አዝ እጅግ የሚምር የሚራራ አምላክ ነውና የእኔ ጌታ ይድረሰው ምሥጋና የእኔ ጌታ ይድረሰው ምሥጋና የእኔ ጌታ ይድረሰው ምሥጋና (፬x)

ጌታ እልሃለሁ አንተን አመልካለሁ (፪x) አምላክ እልሃለሁኝ አንተን አመልካለሁ (፪x) አንተን አመልካለሁ አንተን አመልካለሁ (፪x)

ይገባሃል የአንደበቴ ቃል ይገባሃል የአፌ ምሥጋና ይገባሃል ልዘምርልህ ይገባሃል ላገለግልህ

እኔ አምላክ እልሃለሁኝ አንተን አመልካለሁ (፭x) እስከዛሬ ተመስገን ብያለሁ ተባረክ ብያለሁ አሃ ከፍ በል ብያለሁ እስከዛሬ ተመስገን ብያለሁ ተባረክ ብያለሁ አሃ ከፍ በል ብያለሁ

ደግሞ ዛሬ ዛሬ ምን ልበል ዛሬ ምን ልበል ደግሞ አሁን አሁን ምን ልበል ጌታ አሁን ምን ልበል ደግሞ ዛሬ ዛሬ ምን ልበል ዛሬ ምን ልበል ዛሬ ምን ልበል

ይገባሃል የአንደበቴ ቃል ይገባሃል የአፌ ምሥጋና ይገባሃል ላገለግልህ ይገባሃል ልዘምርልህ

ሃሌሉያ ሃሌሉያ (፬x) ሃሌሉያ ሃሌሉያ (፬x) ሃሌሉያ ሃሌሉያ (፬x)