አይበቃም (Aybeqam) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን
(Kalkidan Tilahun)

Lyrics.jpg


(4)

አትለዋወጥም
(Atelewawetem)

ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃልኪዳን ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Kalkidan Tilahun)

ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ የምለዉ
የጥያቄዬ ፡ መልስ ፡ የሆነዉ
ልቤ ፡ ያረፈበት ፡ ምወደው
እፎይ ፡ የምልበት ፡ እርሱ ፡ ነዉ (፪x)

አይበቃም ፡ እንደዚህ ፡ ብለህ
አይበቃም ፡ እንደዚያም ፡ ብለህ
አይበቃም ፡ እኔ ፡ ባመልክህ
አይበቃም ፡ አይበቃም ፣ አይበቃም ፡ አይበቃም

አምላክ ፡ ሆይ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ የለም (፬x)

የማለዳ ፡ ጨረር ፡ የጠዋት ፡ ብርሃን
አንተ ፡ በደስታ ፡ አሞከው ፡ ልቤን
ህልሜን ፡ ልተርከው፡ ከእንቅልፌ ፡ ስነቃ
አረጋገጥክልኝ ፡ ሌሊቱ ፡ እንዳበቃ (፪x)

ምን ፡ ዓይነት ፡ አምላክ ፡ ነህ
ምን ፡ ዓይነት ፡ ንጉሥ ፡ ነህ (፪x)

ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ የምለዉ
የጥያቄዬ ፡ መልስ ፡ የሆነዉ
ልቤ ፡ ያረፈበት ፡ ምወደው
እፎይ ፡ የምልበት ፡ እርሱ ፡ ነዉ (፪x)

አይበቃም ፡ እንደዚህ ፡ ብለህ
አይበቃም ፡ እንደዚያም ፡ ብለህ
አይበቃም ፡ እኔ ፡ ባመልክህ
አይበቃም ፡ አይበቃም ፣ አይበቃም ፡ አይበቃም

አምላክ ፡ ሆይ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ የለም (፬x)

ማምለክ ፡ አየሬ ፡ ነው ፡ ሳላመልክ፡ አልኖርም
ከሁኔታ ፡ ጋር ፡ አላያይዘውም
ተመስገን ፡ ሳልልህ ፡ ሥምህን ፡ ሳልቀድስ
እንዴት ፡ እኖራለሁ ፡ እኔ ፡ ሳልተነፍስ (፪x)

ምን ፡ ዓይነት ፡ አምላክ ፡ ነህ
ምን ፡ ዓይነት ፡ ንጉሥ ፡ ነህ (፪x)

አምላክ ፡ ሆይ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ የለም (፬x)

አይበቃም ፡ እንደዚህ ፡ ብለህ
አይበቃም ፡ እንደዚያም ፡ ብለህ
አይበቃም ፡ እኔ ፡ ባመልክህ
አይበቃም ፡ አይበቃም ፣ አይበቃም ፡ አይበቃም

እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ስለ ፡ ሥምህ ፡ አመልክሃልሁ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ስለ ፡ ራስህ ፡ አመልክሃልሁ ፡ አሃ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ስለ ፡ ሥምህ ፡ አመልክሃልሁ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ስለ ፡ ራስህ ፡ አመልክሃልሁ ፡ አሃ (፪x)