አትለዋወጥም (Atelewawetem) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን
(Kalkidan Tilahun)

Lyrics.jpg


(4)

አትለዋወጥም
(Atelewawetem)

ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃልኪዳን ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Kalkidan Tilahun)

የነበረ ፡ ያለ ፡ የሚኖር ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ በመደነቅ ፡ የሚከታተለው (፪x)

የነበረው ፡ ሁሉ ፡ በነበር ፡ አለቀ
የድሮ ፡ ታሪክ ፡ ነው ፡ እጅጉን ፡ የራቀ
ድሮም ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ነበረ ፡ ኃያል ፡ ሆኖ
በዘመናት ፡ መሃል ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው

የነበረ ፡ ያለ ፡ የሚኖር ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ በመደነቅ ፡ የሚከታተለው (፪x)

አዝ፦ አንተ ፡ አትለዋወጥም ፡ አሃ
አንተ ፡ ኃይልህ ፡ አይቀንስም ፡ አዎ
አንተ ፡ ዘመንህ ፡ አያልቅም ፡ አሃ
አንተ ፡ ጉልበትህ ፡ አይዝልም ፡ አሃ (፪x)

አትለዋወጥም ፡ አሃሃ (፲፮x)

እኔ ፡ እኮ ፡ የሚገርመኝ ፡ ሁልጊዜ ፡ ያው ፡ መሆንህ ፡ ነው (፪x)
እኔ ፡ እኮ ፡ የሚደንቀኝ ፡ ሁልጊዜ ፡ ያው ፡ መሆንህ ፡ ነው (፰x)

አዝ፦ አንተ ፡ አትለዋወጥም ፡ አሃ
አንተ ፡ ኃይልህ ፡ አይቀንስም ፡ አዎ
አንተ ፡ ዘመንህ ፡ አያልቅም ፡ አሃ
አንተ ፡ ጉልበትህ ፡ አይዝልም ፡ አሃ (፪x)

አትለዋወጥም ፡ አሃሃ (፲፮x)

አይተናል ፡ አዎ ፡ ኃያላን ፡ ሲያልፉ
አይተናል ፡ አዎ ፡ ብርቱዎች ፡ ሲደክሙ
አይተናል ፡ አዎ ፡ ቁንጅና ፡ ሲያልፍ
አይተናል ፡ አዎ ፡ ውበት ፡ ሲረግፍ (፪x)

አዝ፦ አንተ ፡ አትለዋወጥም ፡ አሃ
አንተ ፡ ኃይልህ ፡ አይቀንስም ፡ አዎ
አንተ ፡ ዘመንህ ፡ አያልቅም ፡ አሃ
አንተ ፡ ጉልበትህ ፡ አይዝልም ፡ አሃ (፪x)

አትለዋወጥም ፡ አሃሃ (፲፮x)

እነ ፡ ኃያላን ፡ እነ ፡ አለቆች
እነ ፡ ነገሥታት ፡ እነ ፡ አልሞት ፡ ባዮች
አንድ ፡ በአንድ ፡ ሁሉም ፡ ሁሉም ፡ አለፉ
እያየናቸው ፡ ከምድር ፡ ላይ ፡ ጠፉ (፪x)

አንተ ፡ ግን ፡ አትለዋወጥም ፡ አሃ
አምላኬ ፡ አትለዋወጥም ፡ አሃ
አምላክህ ፡ አይለዋወጥም ፡ አሃ
አምላክሽ ፡ አይለዋወጥም ፡ አሃ

እርሱ ፡ እኮ ፡ አይለዋወጥም ፡ አሃ
አምላኬ ፡ አይለዋወጥም ፡ አሃ
አምላክህ ፡ አይለዋወጥም ፡ አሃ
አምላክሽ ፡ አይለዋወጥም ፡ አሃ

አትለዋወጥም ፡ አሃሃ (፲፮x)

ትልቅ ፡ ነህ ፡ ሰፊ ፡ ነህ ፡ ጥልቅ ፡ ነህ ፡ ረቂቅ (፪x)

በዓይኔ ፡ በብረቱ ፡ አይቻለሁ ፡ አሃ
ትልቅነትህን ፡ አይቻለሁ ፡ አሃ
የማይሆነው ፡ ሲሆን ፡ አይቻለሁ ፡ አሃ
ያለቀ ፡ ሲጀምር ፡ አይቻለሁ ፡ አሃ (፪x)

ስለዚህ/እኔማ ፡ አምልክሃለሁ
ወገቤን ፡ ታጥቄ ፡ አምልክሃለሁ
ልክህን ፡ አውቄ ፡ አምልክሃለሁ
ልክህን ፡ አውቄ (፬x)