አምላኬ ፡ ሆይ (Amlakie Hoy) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን
(Kalkidan Tilahun)

Lyrics.jpg


(4)

አትለዋወጥም
(Atelewawetem)

ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃልኪዳን ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Kalkidan Tilahun)

ሞቷል ፡ ብዬ ፡ አፈር ፡ ሳለብሰው
ለካ ፡ አምላኬ ፡ ከሞት ፡ በላይ ፡ ነው
ለካ ፡ አምላኬ ፡ ከሞት ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)

አምላኬ ፡ ሆይ ፡ አደንቅሃለው
ሌላ ፡ ነገር ፡ አይደለም ፡ ይሄስ ፡ ታምር ፡ ነው
ይኸው ፡ ቆሞ ፡ ይሄዳል ፡ ሞተ ፡ የተባለው (፬x)

አንተን ፡ ጠርቶ ፡ ማን ፡ ዘገየ
ከሰው ፡ ሁሉ ፡ የተለየ
አንተን ፡ ብሎ ፡ ማን ፡ አፈረ
ማን ፡ ከሰረ ፡ ማን ፡ ከሰረ (፪x)

ሞቷል ፡ ብዬ ፡ አፈር ፡ ሳለብሰው
ለካ ፡ አምላኬ ፡ ከሞት ፡ በላይ ፡ ነው
ለካ ፡ አምላኬ ፡ ከሞት ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)

አምላኬ ፡ ሆይ ፡ አደንቅሃለው
ሌላ ፡ ነገር ፡ አይደለም ፡ ይሄስ ፡ ታምር ፡ ነው
ይኸው ፡ ቆሞ ፡ ይሄዳል ፡ ሞተ ፡ የተባለው (፪x)

አንተን ፡ ጠርቶ ፡ ማን ፡ ዘገየ
ከሰው ፡ ሁሉ ፡ የተለየ
አንተን ፡ ብሎ ፡ ማን ፡ አፈረ
ማን ፡ ከሰረ ፡ ማን ፡ ከሰረ (፪x)

ኦ ፡ ነፍሴን ፡ አዳናት
ኦ ፡ ከእሳት ፡ አወጣት
ኦ ፡ እስሯን ፡ ፈቶ
ኦ ፡ ነጻ ፡ ነሽ ፡ አላት (፪x)

አምላኬ ፡ ታድጐኛል
ዜግነቴን ፡ ለውጦታል
ቋንቋዬን ፡ ቀይሮታል
ሠማያዊ ፡ አድርጐታል (፪x)

ኦ ፡ ነፍሴን ፡ አዳናት
ኦ ፡ ከእሳት ፡ አወጣት
ኦ ፡ እስሯን ፡ ፈቶ
ኦ ፡ ነጻ ፡ ነሽ ፡ አላት (፪x)

የሚያስብልኝ ፡ አለኝ
የውስጤን ፡ የሚያውቅልኝ
የእሳቱን ፡ ቅጥር ፡ ሰርቶ
ይጠብቀኛል ፡ ተግቶ