አመልካለሁ (Amelkalehu) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን
(Kalkidan Tilahun)

Lyrics.jpg


(4)

አትለዋወጥም
(Atelewawetem)

ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃልኪዳን ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Kalkidan Tilahun)

አመልካለሁ ፡ እጆቼን ፡ አንስቼ
ጥያቄዬን ፡ ሁሉ ፡ እረስቼ
ዓላማዬ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ከቶ ፡ አልሄድም ፡ ክበር ፡ ሳልልህ
ዓላማዬ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ከቶ ፡ አልሄድም ፡ ክበር ፡ ሳልልህ (፪x)

ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፬x)

ሁልጊዜ ፡ ሥምህን ፡ እጠራለሁ ፡ እጠራለሁ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ እልሃለሁ ፡ እልሃለሁ (፪x)

እልሃለሁ ፡ እልሃለሁ ፣ እልሃለሁ ፡ እልሃለሁ

ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፬x)

እንደ ፡ ማር ፡ ጣፈጠኝ ፡ ሥምህ ፡ አፌ ፡ ላይ
ከሥምህ ፡ የሚበልጥ ፡ ሥም ፡ ይገኛል ፡ ወይ (፪x)
ሥሞች ፡ ተሰብስበው ፡ ለሥምህ ፡ ሰገዱ
ከሥማቸው ፡ ይልቅ ፡ ሥምህን ፡ ወደዱ (፪x)

ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፬x)

ምስጢሩ ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ምስጢሩ ፡ ይኼ ፡ ነው
ሥሙን ፡ ያስወደደው ፡ በሃሪው ፡ እኮ ፡ ነው (፪x)
ሥሙና ፡ ሕይወቱ ፡ አንድ ፡ ላይ ፡ ይሄዳል
እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለ ፡ ከወዴት ፡ ይገኛል (፪x)

ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፬x)

እሺ ፡ ባይነትህ ፡ ታዛዥነትህ
ክብርህን ፡ ለመጣል ፡ ክብር ፡ መጣልህ (፪x)
ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ማለትህ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አድርጐሃል
ከሥሞች ፡ የሚበልጥ ፡ ሥምን ፡ አሰጥቶሃል (፪x)

ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፬x)

አመልካለሁ ፡ እጆቼን ፡ አንስቼ
ጥያቄዬን ፡ ሁሉ ፡ እረስቼ
ዓላማዬ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ከቶ ፡ አልሄድም ፡ ክበር ፡ ሳልልህ
ዓላማዬ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ከቶ ፡ አልሄድም ፡ ክበር ፡ ሳልልህ

ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፬x)

ምነው ፡ ነፍሴ ፡ እንደ ፡ ውኃ ፡ በሆንልኝ
አምላኬ ፡ ፊት ፡ እንደ ፡ ጅረት ፡ ቢፈስልኝ (፪x)