ያላንተ ፡ ኑሮ (Yalante Nuro) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ያላንተ ፡ ኑሮ ፡ አይሆንልኝም ፡ ጌታዬ ፡ አይሆንልኝም
እኔስ ፡ ያላንተ ፡ አይሆንልኝም ፡ ጌታዬ ፡ አይሆንልኝም

ወጣሁ ፡ ወረድኩ ፡ ብዙ ፡ አየሁኝ
እንዳንተ ፡ የሚሆን ፡ መቼ ፡ አገኘሁኝ
ድካሜ ፡ ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ነበረ
አንተ ፡ ስትመጣ ፡ ሕይወቴ ፡ አማረ

አዝ፦ ታዲያ ፡ ያላንተ ፡ እንዴት ፡ አድርጌ ፡ እኖራለሁ ፡ እንዴት ፡ አድርጌ
ያላንተ ፡ ኑሮ ፡ አይሆንልኝም ፡ ጌታዬ ፡ አይሆንልኝም

የዓለም ፡ ፍቅር ፡ ተሟጦ ፡ ያልቃል
ያንተ ፡ ፍቅር ፡ ግን ፡ መቼ ፡ ያረጃል
አትጠገብም ፡ ቀርቦ ፡ ላየህ
አቤት ፡ ጌታዬ ፡ ምን ፡ አይነት ፡ ነህ

አዝ፦ ታዲያ ፡ ያላንተ ፡ እንዴት ፡ አድርጌ ፡ እኖራለሁ ፡ እንዴት ፡ አድርጌ
ያላንተ ፡ ኑሮ ፡ አይሆንልኝም ፡ ጌታዬ ፡ አይሆንልኝም

የአሕዛብ ፡ ኑሮ ፡ ሁሌ ፡ ይደንቀኛል
ሰው ፡ ካለ ፡ ኢየሱስ ፡ እንዴት ፡ ይኖራል
አንተን ፡ ያጣ ፡ ሰው ፡ ያልታደለ ፡ ነው
ከርታታ ፡ መና ፡ ተስፋ ፡ የሌለው

አዝ፦ እኔስ ፡ ኑሮ ፡ አይሆንልኝም ፡ ጌታዬ ፡ አይሆንልኝም
እኔስ ፡ ያላንተ ፡ አይሆንልኝም ፡ ኢየሱስ ፡ አይሆንልኝም