From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ማራናታ (፫x)
ቶሎ ፡ ና ፤ የኔ ፡ ጌታ ፤ የኔ ፡ ጌታ (፪x)
ቃልህን ፡ በመግለጥ፧ ፡ ዓለምን ፡ ሙላና
በድንቅ ፡ በተዓምር ፡ ተመላለስና
አንተን ፡ ተቀብለው ፡ ነፍሳት ፡ ይዳኑና
የኔ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ እባክህ ፡ ቶሎ ፡ ና
አዝ፦ ማራናታ (፫x)
ቶሎ ፡ ና ፤ የኔ ፡ ጌታ ፤ የኔ ፡ ጌታ
እመጣለሁ ፡ ብለህ ፡ ቃል ፡ ገብተህልናል
ቃልህ ፡ እንዲፈጸም ፡ ልጆችህ ፡ ናፍቀናል
የታረደውን ፡ በግ ፡ ስለበደላችን
ልናይ ፡ እንወዳለን ፡ ሁላችን ፡ በዓይናችን
አዝ፦ ማራናታ (፫x)
ቶሎ ፡ ና ፤ የኔ ፡ ጌታ ፤ የኔ ፡ ጌታ
በዕንቁ ፡ በወርቅ ፡ አርጐ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሰራት
ጥላቻ ፡ ተረስቶ ፡ ፍቅር ፡ የሞላባት
ለእኛ ፡ ለልጆቹ ፡ አምላክ ፡ ያዘጋጃት
ኢየሩሳሌምን ፡ መቼ ፡ ነው ፡ የማያት
አዝ፦ ማራናታ (፫x)
ቶሎ ፡ ና ፤ የኔ ፡ ጌታ ፤ የኔ ፡ ጌታ (፪x)
|