ማነው ፡ ማነው (Manew Manew) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በኪሩቤል ፡ ላይ ፡ የተቀመጠው
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ታላቅ ፡ የሆነው
ከዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ውረድ ፡ የሚለው
እሱን ፡ ተክቶ ፡ የሚቆም ፡ ማነው

አዝማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x)
ከአምላክ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው
ማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x)
ከአንተ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው

ውሆች ፡ በእፍኙ ፡ የሰፈረው
ሰማይ ፡ በስንዝሩ ፡ የለካው
በምን ፡ ምሣሌ ፡ እንመስለው
ይህን ፡ እግዚአብሔር ፡ ማን ፡ እንበለው

አዝማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x)
ከአምላክ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው
ማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x)
ከአንተ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው

ባህርን ፡ ከፍሎ ፡ የሚያሻግረው
ሰማይን ፡ ከፍቶ ፡ መና ፡ የሚያወርደው
በጸናች ፡ ክንዱ ፡ የሚታደገው
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው

አዝማነው ፡ ማነው ፡ እንደእርሱ ፡ ማነው (፪x)
ከእርሱስ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው
ማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x)
ከአንተ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው

ክንዱ ፡ አይዝልም ፡ የምናመልከው
ሁሌ ፡ ብርቱ ፡ ነው ፡ የማይታክተው
ይሄ ፡ አምላካችን ፡ ዛሬም ፡ ሕያው ፡ ነው
ተወዳዳሪ ፡ መሳይ ፡ የሌለው

አዝማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው(፪x)
ከአንተ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው
ማነው ፡ ማነው ፡ እንደእርሱ ፡ ማነው (፪x)
ከእርሱስ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው

በነፃ ፡ ብሉ ፡ ጠጡ ፡ የሚለው
ዋጋ ፡ ማይጠይቅ ፡ ማያስከፍለው
አንድያ ፡ ልጁን ፡ ወዶ ፡ ሚሰጠው
ከእግዚአብሔር ፡ በቀር ፡ ወዳጅስ ፡ ማነው

አዝማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x)
ከአንተ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው
ማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x)
ከአንተ ፡ በቀር ፡ ወዳጅስ ፡ ማነው

ሁሉን ፡ ይቀርባል ፡ እሩህሩህ ፡ ነው
እንደሰው ፡ አይደል ፡ አይሰለቸው
ወረትን ፡ አያውቅ ፡ ጊዜ ፡ አይለውጠው
እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው

አዝማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x)
ከአምላክ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው
ማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x)
ከአንተ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው (፫x)