ለሰው ፡ አላወራም (Lesew Alaweram) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ለሰው ፡ አላወራም ፡ ምን ፡ ትርፍ ፡ አገኛለሁ
ሃዘኔን ፡ ብሶቴን ፡ ላንተው ፡ እነግራለሁ
ደጃፌን ፡ ዘግቼ ፡ አጫውትሃለሁ
አምናለሁ ፡ ካንተ ፡ ዘንድ ፡ ምላሽ ፡ አገኛለሁ (፪x)

አዝ፦ የሚያስጨንቀኝን ፡ ላንተው ፡ እነግራለሁ
ትካዜዬን ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ እጥላለሁ
የመድኃኒቴ ፡ አምላክ ፡ ተስፋ ፡ አረግሃለሁ (፪x)

የኤርትራን ፡ ባህር ፡ ታሻግረኛለህ
ከሰማያት ፡ መናን ፡ ታወርድልኛለህ
ሃሳብህም ፡ ከቶ ፡ አይከለከልም
ሁሉ ፡ ይቻልሃል ፡ ምንም ፡ አይከብድህም (፪x)

አዝ፦ የሚያስጨንቀኝን ፡ ላንተው ፡ እነግራለሁ
ትካዜዬን ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ እጥላለሁ
የመድኃኒቴ ፡ አምላክ ፡ ተስፋ ፡ አረግሃለሁ (፪x)

የነገሩህንም ፡ የማትረሳ ፡ ነህ
አንዱም ፡ አይጠፋህም ፡ ታስታውሰዋለህ
ሕመሜን ፡ በሙሉ ፡ አንተ ፡ ታውቀዋለህ
መድኃኒቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ትፈውሰኛለህ (፪x)

አዝ፦ የሚያስጨንቀኝን ፡ ላንተው ፡ እነግራለሁ
ትካዜዬን ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ እጥላለሁ
የመድኃኒቴ ፡ አምላክ ፡ ተስፋ ፡ አረግሃለሁ (፪x)

::የመድኃኒቴ ፡ አምላክ ፡ ተስፋ ፡ አረግሃለሁ (፫x)