ጌታ ፡ ይሻልሃል (Gieta Yeshalehal) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ጣል ፡ ጣል ፡ አታርጊው ፡ ኢየሱስን ፡ ውደጂው (፪x)
ደግሞም ፡ አትናቂው ፡ ክብርን ፡ ለሱ ፡ ስጪው (፪x)
ዓይንሽ ፡ ያረፈበት ፡ እሱ ፡ ያጠፋሻል (፪x)
ተይ ፡ ተይ ፡ አትወላውይ ፡ ጌታ ፡ ይሻልሻል (፪x)

አዝ፦ ጌታ ፡ ይሻልሻል ፡ ጌታ ፡ ይሻልሻል ፡ ኢየሱስ ፡ ይሻልሻል
ኢየሱስ ፡ ይሻልሃል ፡ ኢየሱስ ፡ ይሻልሃል ፡ ጌታ ፡ ይሻልሃል

ነገ ፡ ዛሬ ፡ አትበል ፡ ኢየሱስን ፡ ተቀበል (፪x)
የሚያባብልህን ፡ ዓለምን ፡ እምቢ ፡ በል (፪x)
ከታሰርክበትም ፡ እርሱ ፡ ይፈታሃል (፪x)
ቀረብ ፡ በል ፡ ተጠጋ ፡ ጌታ ፡ ይሻልሃል (፪x)

አዝ፦ ጌታ ፡ ይሻልሻል ፡ ጌታ ፡ ይሻልሻል ፡ ኢየሱስ ፡ ይሻልሻል
ኢየሱስ ፡ ይሻልሃል ፡ ኢየሱስ ፡ ይሻልሃል ፡ ጌታ ፡ ይሻልሃል

የሚያታልለውን ፡ የሱን ፡ ቃል ፡ አትስሚ (፪x)
ይልቅስ ፡ ከአምላክሽ ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ተስማሚ (፪x)
ሊሰርቅና ፡ ሊያድ ፡ ሊያጠፋሽ ፡ ነውና (፪x)
ነይ ፡ ነይ ፡ ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ እሱን ፡ ተይውና (፪x)

አዝ፦ ጌታ ፡ ይሻልሻል ፡ ጌታ ፡ ይሻልሻል ፡ ኢየሱስ ፡ ይሻልሻል
ኢየሱስ ፡ ይሻልሃል ፡ ኢየሱስ ፡ ይሻልሃል ፡ ጌታ ፡ ይሻልሃል

እስኪ ፡ ወንድሜ ፡ ሆይ ፡ ተስፋህ ፡ ምንድነው (፪x)
ምንም ፡ ነገር ፡ የለ ፡ እስኪ ፡ አስበው (፪x)
በዚህ ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ ሰብሰብ ፡ በልና (፪x)
አረፍ ፡ በል ፡ ተቀመጥ ፡ ኢየሱስን ፡ ያዝና (፪x)

አዝ፦ ጌታ ፡ ይሻልሃል ፡ ጌታ ፡ ይሻልሃል፡ ኢየሱስ ፡ ይሻልሃል
ኢየሱስ ፡ ይሻልሻል ፡ ኢየሱስ ፡ ይሻልሻል ፡ ጌታ ፡ ይሻልሻል