From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ እፁብ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አንተ ፡ አትለወጥም
ግሩም ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ስራህም ፡ አያልቅም (፪x)
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በማደሪያው
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በዙፋኑ (፪x)
ሰማይ ፡ ዙፋንህ ፡ ነው ፡ ምድር ፡ መረገጫ
አለም ፡ ዙፋንህ ፡ ነው ፡ ያንተ ፡ መቀመጫ
ሰማይም ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ ምድርም ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ ሁሉ ፡ ግዛትህ ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በማደሪያው
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በዙፋኑ (፪x)
አዝ፦ እፁብ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አንተ ፡ አትለወጥም
ግሩም ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ስራህም ፡ አያልቅም (፪x)
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በማደሪያው
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በዙፋኑ (፪x)
ይሁን ፡ ይሁን ፡ ብለህ ፡ የፈጠርከው ፡ ሁሉ
ጻድቅነትህን ፡ ይመሰክራሉ
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ እወቁት ፡ ይላሉ ፡ አክብሩት ፡ ይላሉ
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በማደሪያው
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በዙፋኑ (፪x)
አዝ፦ እፁብ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አንተ ፡ አትለወጥም
ግሩም ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ስራህም ፡ አያልቅም (፪x)
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በማደሪያው
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በዙፋኑ (፪x)
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለውን ፡ በሃይሉ ፡ አዋርዶ
የሃያላንንም ፡ ቀስታቸውን ፡ ሰብሮ
በክብር ፡ ይኖራል ፡ ዘላለም ፡ ይገዛል ፡ ዙፋኑ ፡ ይጸናል
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በማደሪያው
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በዙፋኑ (፪x)
አዝ፦ እፁብ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አንተ ፡ አትለወጥም
ግሩም ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ስራህም ፡ አያልቅም (፪x)
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በማደሪያው
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በዙፋኑ ፡ (፪x)
በዘላለም ፡ ፍቅሩ ፡ ቀድሞ ፡ ባቀደው
አለምን ፡ ሊያድናት ፡ ኢየሱስን ፡ ላከው
ሃሳቡ ፡ ጸንታለች ፡ ማዳኑን ፡ አይተናል
ከሀጥያት ፡ እስራት ፡ ከሞትም ፡ ድነናል
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በማደሪያው
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በዙፋኑ (፪x)
አዝ፦ እፁብ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አንተ ፡ አትለወጥም
ግሩም ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ስራህም ፡ አያልቅም (፪x)
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በማደሪያው
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በዙፋኑ (፪x)
ዙሪያው ፡ ገደል ፡ ሆኖ ፡ ግራ ፡ ቢገባህም
ጨለማው ፡ አይሎ ፡ መውጫው ፡ ቢጠፋም
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ እሱ ፡ አይተውህም ፡ እሱ ፡ አይጥልህም
ዙሪያው ፡ ገደል ፡ ሆኖ ፡ ግራ ፡ ቢገባሽም
ጨለማ ፡ አይሎ ፡ መውጫ ፡ ቢጠፋሽም
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ እሱ ፡ አይተውሽም ፡ እሱ ፡ አይጥልሽም
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በማደሪያው
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በዙፋኑ (፪x)
አዝ፦ እፁብ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አንተ ፡ አትለወጥም
ግሩም ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ስራህም ፡ አያልቅም (፪x)
|