Kalkidan Tilahun/Abietu Gulbetie Hoy Ewedihalehu/Ametat Aylewetuhem

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ቃልኪዳን ጥላሁን ርዕስ አመታት አይለውጡህም አልበም አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ

አመታት አመታት አንተን አይለውጡህም (፪x) ዘመናት ዘመናት አንተን አይለውጡህም (፪x)

ጥንትም ያለህ ዛሬም ለዘላለም አምረህ ደምቀህ አሸብርቀህ በዙፋንህ ላይ ጌታ ትኖራለህ አምረህ ደምቀህ አሸብርቀህ የአብርሃም አምላክ ዛሬም አላረጀህ አምረህ ደምቀህ አሸብርቀህ የይስሃቅ አምላክ ዛሬም አላረጀህ የያዕቆብ አምላክ ዛሬም አላረጀህ

ስንቶቹ ነገሥታቶች ሲያልፉ ሲሻሩ የእኛ አምላክ ብቻውን አለ በክብሩ የነገሥታቶች ንጉሥ የጌቶች ጌታ አይደክመው አይታክተው ሁሉን ሊረታ

አመታት አመታት አንተን አይለውጡህም (፪x) ዘመናት ዘመናት አንተን አይለውጡህም (፪x)

ጥንትም ያለህ ዛሬም ለዘላለም አምረህ ደምቀህ አሸብርቀህ በዙፋንህ ላይ ጌታ ትኖራለህ አምረህ ደምቀህ አሸብርቀህ ፡ የአብርሃም አምላክ ዛሬም አላረጀህ አምረህ ደምቀህ አሸብርቀህ የይስሃቅ አምላክ ዛሬም አላረጀህ የያዕቆብ አምላክ ዛሬም አላረጀህ

በእነ አብርሃም ዘመን የነበረው ሕዝቡን በምድረ በዳ የሚመራው የዳዊት የሙሴ አምላክ መች ደከመው የቀን የወሩ ብዛት አልለወጠው

አመታት አመታት አንተን አይለውጡህም (፪x) ዘመናት ዘመናት አንተን አይለውጡህም (፪x)

ጥንትም ያለህ ዛሬም ለዘላለም አምረህ ደምቀህ አሸብርቀህ በዙፋንህ ላይ ጌታ ትኖራለህ አምረህ ደምቀህ አሸብርቀህ የአብርሃም አምላክ ዛሬም አላረጀህ አምረህ ደምቀህ አሸብርቀህ የይስሃቅ አምላክ ዛሬም አላረጀህ የያዕቆብ አምላክ ዛሬም አላረጀህ

በሐዋርያት ነብያት ድንቅ የሰራው መስራት አያቅተውም ዛሬም ያው ነው የአጋንንትን ምሽግ ያፈራርሳል ከጥንቱ የበለጠ ዛሬም ይሰራል

አመታት አመታት አንተን አይለውጡህም (፪x) ዘመናት ዘመናት አንተን አይለውጡህም (፪x)

ጥንትም ያለህ ዛሬም ለዘላለም አምረህ ደምቀህ አሸብርቀህ በዙፋንህ ላይ ጌታ ትኖራለህ (፬x)

የአብርሃም አምላክ ዛሬም አላረጀህ የይስሃቅ አምላክ ዛሬም አላረጀህ የያዕቆብ አምላክ ዛሬም አላረጀህ የያዕቆብ አምላክ ዛሬም አላረጀህ