ርዕስ (Title) - ቃልኪዳን ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

link={{{Artist}}}/{{{Album}}}


(Volume)

አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ
(Album)

ቁጥር (Track):

(Track)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃልኪዳን ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by {{{Artist}}})

በዙሪያዬ ሆኖ ጠላት ሲያውከኝ
ያሸነፈ መስሎ ሲፎክርብኝ
በጨነቀኝ ጊዜ ወዳንተ ጮህኩኝ
ሰማይን ዝቅ አርገህ ከተፍ አልክልኝ

አዝ
አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ
አቤቱ የእኔ ጌታ እወድሃለሁ
እግዚአብሔር አለቴ አምባ መድኃኒቴ
የምታመንበት ሆነኝ እረዳቴ (፪x)

እጆቼን አንስቼ ተገፋው አልኩኝ
እግዚአብሔር ከሰማይ ተበቀለልኝ
ምድር ተናወጠች ቁጣውም ነደደ
በጠላቶቼ ላይ መብረቅ አወረደ

አዝ
አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ
አቤቱ የእኔ ጌታ እወድሃለሁ
እግዚአብሔር አለቴ አምባ መድኃኒቴ
የምታመንበት ሆነኝ እረዳቴ (፪x)

እግሮቼም ቆሙልኝ አልተንሸራተቱም
ጠላቶቼን ያዝኩኝ አላመለጡኝም
በኮረብቶቹም ላይ ለሚያቆመኝ ጌታ
እስኪ ላመስግነው ልዘምር በእልልታ

አዝ
አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ
አቤቱ የእኔ ጌታ እወድሃለሁ
እግዚአብሔር አለቴ አምባ መድኃኒቴ
የምታመንበት ሆነኝ እረዳቴ (፪x)

ለሚታመኑበት እርሱ ጋሻ ነው
ክፉዬን አይወድም ይነዳል ቁጣው
ከመቅደሱ ሆኖ ድምፄን ይሰማኛል
እግዚአብሔርን አይቶ ጠላቴ ፈርቶኛል

አዝ
አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ
አቤቱ የእኔ ጌታ እወድሃለሁ
እግዚአብሔር አለቴ አምባ መድኃኒቴ
የምታመንበት ሆነኝ እረዳቴ (፪x)

አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ
አቤቱ የኔ ጌታ እወድሃለሁ
እግዚአብሔር አለቴ አምባ መድኃኒቴ
የምታመንበት ሆነኝ እረዳቴ (፪x)

[[Category:]]