From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ቢሆንም ፡ ባይሆንም ፡ አምልኮዬን ፡ አላቆምም (፪x)
አዳዲስ ፡ መዝሙር ፡ ለእርሱ ፡ ነውና ፡ (ምሥጋና ፡ ምሥጋና)
ለታላቅነቱ ፡ (ምሥጋና ፡ ምሥጋና) (፪x)
ታሞ ፡ አዘነ ፡ ሞቶ ፡ አለቀሰ
የሰው ፡ እርዳታ ፡ መች ፡ ከዚህ ፡ አለፈ
ሲታመም ፡ ቀርቶ ፡ ሞቶ ፡ ቢደርስ
ሬሳ ፡ አይተናል ፡ ሲቀሰቀስ
ቢሆንም ፡ ባይሆንም ፡ አምልኮዬን ፡ አላቆምም (፪x)
የቤቱን ፡ ትልቅ ፡ ኤልያብን ፡ ትቶ
ቀቡልኝ ፡ ካለ ፡ እረኛውን ፡ ጠርቶ
ያዕቆብን ፡ ወዶ ፡ ኤሳውን ፡ ከጠላ
ሲረፍድ ፡ ይገባል ፡ የጌታ ፡ ስራ
ትክክል ፡ ነው ፡ ትክክል ፡ ነው (፮x)
የሰማይ ፡ መስኮት ፡ ቢከፈት ፡ እንኳን
በአንድ ፡ ቀን ፡ ይሄ ፡ እንዴት ፡ ይሆናል
ንጉሡ ፡ እምቢ ፡ ቢል ፡ ትንቢት ፡ አዳምጦ
ሳይበላ ፡ ሞተ ፡ በሰው ፡ ተረግጦ
ቢሆንም ፡ ባይሆንም ፡ አምልኮዬን ፡ አላቆምም (፪x)
አዳዲስ ፡ መዝሙር ፡ ለእርሱ ፡ ነውና ፡ (ምሥጋና ፡ ምሥጋና)
ለታላቅነቱ ፡ (ምሥጋና ፡ ምሥጋና) (፪x)
ትክክል ፡ ነው ፡ ትክክል ፡ ነው (፮x)
|