From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ፀሐይ ፡ ዘምበል ፡ ብላ ፡ አመሻሹ ፡ ላይ ፡ ነኝ
ችግሬ ፡ እያለ ፡ ሚነጋ ፡ መሰለኝ
ለካ ፡ አምላኬ ፡ ሰምቷል ፡ ጠላቴ ፡ እየዛተ
የተዘጋጋው ፡ በር ፡ አውቆ ፡ ተከፈተ
አዝ:- ሰይጣን ፡ ውሸቱን ፡ ነው (፪x) ፡ ትሞታለህ ፡ ያለው (፪x)
ኢየሱስ ፡ እውነቱን ፡ ነው (፫x) ፡ አትሞትም ፡ ያለው (፪x)
በሞትና ፡ በእኔ ፡ አንድ ፡ እርምጃ ፡ ቀርቶ
ምን ፡ ረዳኝ ፡ አትበል ፡ ከረፈደ ፡ መጥቶ
አምላክህ ፡ ሲነሳ ፡ ሲያንጐዳጉድ ፡ ከላይ
መከራህ ፡ በጓዳ ፡ ክብርህ ፡ በአደባባይ
ይደርደር ፡ ይደርደር ፡ በገና
ዕድሜ ፡ ቀጠለልኝ ፡ ይገባዋልና
ሌላ ፡ ሌላ ፡ ምሥጋና (፬x)
ፈሮን ፡ ከሁአላ ፡ ቀይ ፡ ባሕር ፡ ከፊት ፡ ነው
ግብጽ ፡ አይመለሱም ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ብለው
በአራቱም ፡ አቅጣጫ ፡ ሞት ፡ እየቸኮለ
የገዳዬ ፡ ገዳይ ፡ ከሰማይ ፡ ብቅ ፡ አለ
አዝ:- ሰይጣን ፡ ውሸቱን ፡ ነው (፪x) ፡ ትሞታለህ ፡ ያለው (፪x)
ኢየሱስ ፡ እውነቱን ፡ ነው (፫x) ፡ አትሞትም ፡ ያለው (፪x)
ይደርደር ፡ ይደርደር ፡ በገና
ዕድሜ ፡ ቀጠለልኝ ፡ ይገባዋልና
ሌላ ፡ ሌላ ፡ ምሥጋና (፬x) (፪x)
|