From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
"(ሃሌሉያ) ሉዑል ፡ ሆይ ፡ ማደሪያህ ፡ እንደምን ፡ የተወደዱ ፡ ናቸው
(ሃሌሉያ) ፡ እናመሰግንሃለን (ሃሌሉያ) (፫x) ፡ ማደሪያህ ፡ ውብ ፡ ነው (ሃሌሉያ) (፬x)"
አዝ:- ማደሪያህ ፡ እንዴት ፡ ያማረ ፡ ነው (፪x)
መንፈስህ ፡ እንዴት ፡ ያማረ ፡ ነው (፰x)
የገባውን ፡ ቃልኪዳኑን ፡ ያላጠፈ
ሲሸከመኝ ፡ ለዘመናት ፡ ያልሰነፈ
በድካሜ ፡ የያለኝን ፡ ሳይለውጠው
ስደርስበት ፡ ሁሉንም ፡ እንዳለኝ ፡ ነው (፪x)
አዝ:- ማደሪያህ ፡ እንዴት ፡ ያማረ ፡ ነው (፪x)
መንፈስህ ፡ እንዴት ፡ ያማረ ፡ ነው (፰x)
"ያማረ ፡ ነው ፡ ማደሪያህ
አንተ ፡ ያለህበት ፡ ጌታዬ
ያማረ ፡ ነው ፡ መኖሪያህ ፡ ያማረ ፡ ነው"
የትንቢቱን ፡ ቃል ፡ ሲፈጽመው ፡ በየተራ
ተሳስቶ ፡ አንዴ ፡ ለሰው ፡ መች ፡ አወራ
አወይ ፡ አባት ፡ ኀጢአቴን ፡ ተሸክሞ
በአደባባይ ፡ እወደዋለሁ ፡ ይላል ፡ ቆሞ (፪x)
እንዴት ፡ ከአምልኮ ፡ እነሳለሁ
ከአምልኮ ፡ የሚሻል ፡ ምንድን ፡ ነው
እንዴት ፡ ከጸሎት ፡ እነሳለሁ
ከጸሎት ፡ የሚያስነሳኝ ፡ ምንድን ፡ ነው
እንዴት ፡ መዝሙር ፡ አቆማለሁ
ከመዘመር ፡ የሚሻል ፡ ምንድን ፡ ነው
መዋያዬ ፡ ቅድስተ ፡ ቅዱሳን
ማደሪያዬ ፡ ቅድስተ ፡ ቅዱሳን (፰x)
|