እድለኛ ፡ ነኝ (Edelegna Negn) - ቃለአብ ፡ ፀጋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቃለአብ ፡ ፀጋዬ
(Kaleab Tsegaye)

Kaleab Tsegaye 1.jpeg


(1)

እንዲህም ፡ አለ
(Endihem Ale)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(Track)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃለአብ ፡ ፀጋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Kaleab Tsegaye)

 
አዝ:- እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ (፪x) እድለኛ
አዲስ ፡ እድሜ ፡ ከሰማይ ፡ የሰጠኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ እድለኛ
እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ አዲስ ፡ እድሜ ፡ ከሰማይ ፡ የሰጠኛ
ለአምልኮ ፡ ማን ፡ ይቀድመኛል

መስቀሉ ፡ ለእኔ ፡ ነው ፡ የተሰራልኝ
ስሞት ፡ ህዝብ ፡ ሊያየኝ ፡ ሊሳለቅብኝ
ለካ ፡ ተዐምራት ፡ በጣም ፡ የሚያምረው
እግዚአብሔር ፡ ከሰማይ ፡ ሲያረፋፍድ ፡ ነዉ

ባልጠፋ ፡ ሰዓት ፡ በሌሊት ፡ ተነስቶ
ያገላብጥ ፡ ጀመር ፡ መዝገቤን ፡ ጐትቶ
የፋርስና ፡ ሜዶን ፡ ህግ ፡ ተገልብጧል
ሃማ ፡ መሞቻዉን ፡ አሳምሮ ፡ ሰርቷል

የሚሞተውን ፡ ሰው ፡ አትሞትም ፡ ብሎታል
የመኖሪያ ፡ ፈቃድ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰጥቶታል
በእርሱ ፡ እድሜ ፡ አይቀለድም (፬x)

በራዕዩ ፡ ምክንያት ፡ ጉድጓድ ፡ ውስጥ ፡ ቢጣልም
እግዚአብሔር ፡ አላለም ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ አይቀርም
መቼ ፡ ጓዳ ፡ ቀረ ፡ በጉድጓድ ፡ ተውጦ
አደባባይ ፡ ወጥቷል ፡ ነገር ፡ ተገልብጦ

በግብጽ ፡ በአካባቢው ፡ በአገር ፡ ሰው ፡ እያለ
ተሸጦ ፡ የመጣው ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ቁጭ ፡ አለ
ፈርኦን ፡ በቤቱ ፡ ቢኖርም ፡ ባይኖርም
ጌታ ፡ ንጉሥ ፡ ካለህ ፡ መሾምህ ፡ አይቀርም

አዝ:- እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ (፪x) እድለኛ
አዲስ ፡ እድሜ ፡ ከሰማይ ፡ የሰጠኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ እድለኛ
እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ አዲስ ፡ እድሜ ፡ ከሰማይ ፡ የሰጠኛ
ለአምልኮ ፡ ማን ፡ ይቀድመኛል (፪x)

እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ አዲስ ፡ እድሜ ፡ ከሰማይ ፡ የሰጠኛ
ለአምልኮ ፡ ማን ፡ ይቀድመኛል