አመቱ ፡ የኔ ፡ ነው (Ametu Yenie New) - ቃለአብ ፡ ፀጋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቃለአብ ፡ ፀጋዬ
(Kaleab Tsegaye)

Kaleab Tsegaye 1.jpeg


(1)

እንዲህም ፡ አለ
(Endihem Ale)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(Track)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃለአብ ፡ ፀጋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Kaleab Tsegaye)

የቅባቱ ፡ ስርዐት ፡ ወዲያው ፡ እንዳለቀ
መች ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ወጣ ፡ ሄደ ፡ በግ ፡ ጠበቀ
ምድረ ፡ በዳ ፡ ለፍቶ ፡ ንጉሥ ፡ ካደረገው
ለተጠቀመበት ፡ መከራም ፡ እድል ፡ ነው

አዝ:- መብቴ ፡ ነው (፪x) ፡ መግባትስ ፡ መብቴ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ስላለ ፡ አመቱ ፡ የኔ/የአንተ ፡ ነው (፪x)
አመቱ ፡ የኔ ፡ ነው (፬x)

በሰፈር ፡ አላልፍም ፡ አፍሬያለሁ ፡ ያልከው
የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ለአንተ ፡ አልቋል ፡ ቀና ፡ በል ፡ ነው
ለእግዚአብሔር ፡ ዘምሩ ፡ ብድር ፡ ያለባችሁ
ድንገት ፡ በኢየሱስ ፡ የተከፈለላቹህ

አዝ:- መብትህ ፡ ነው (፪x) ፡ ወግማ ፡ መብትህ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ የባረ ፡ ዘበረ ፡ ታየ ፡ ይኀው??? (፪x)
ዘበረ ፡ ታየ ፡ ይኀው (፬x)

ሰፈሩን ፡ ቢዞሩት ፡ ቢሽከረከሩት
ዘልቀው ፡ እንዳይገቡ ፡ በእሳት ፡ ቀጥሮት
ሟርተኛም ፡ በለአም ፡ ተራራ ፡ ይዞራል
እስራኤል ፡ በድንኳን ፡ አምሮበት ፡ ቁጭ ፡ ብሏል

አዝ:- መብቴ ፡ ነው (፪x) ፡ መግባትስ ፡ መብቴ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ስላለ ፡ አመቱ ፡ የአንተ ፡ ነው (፪x)
አመቱ ፡ የእኔ ፡ ነው (፬x)

መብትህ ፡ ነው (፪x) ፡ ወግማ ፡ መብትህ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ የባረ ፡ ዘበረ ፡ ታየ ፡ ይኀው (፪x)
ዘበረ ፡ ታየ ፡ ይኀው (፮x)