አልሞትኩም (Almotkum) - ቃለአብ ፡ ፀጋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቃለአብ ፡ ፀጋዬ
(Kaleab Tsegaye)

Kaleab Tsegaye 1.jpeg


(1)

እንዲህም ፡ አለ
(Endihem Ale)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(Track)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃለአብ ፡ ፀጋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Kaleab Tsegaye)

አይሁዶች ፡ ሃሳባቸው ፡ በሃማ ፡ እጅ ፡ መጥፋታቸው (፪x)
ማን ፡ እንደሚሞት ፡ ላልታወቀ ፡ መስቀያው ፡ ተሰርቶ ፡ አለቀ
ጆሮውን ፡ ለሰማይ ፡ ሰጥቶ ፡ የምድሩን ፡ ለሃማ ፡ ትቶ
ከአባቱ ፡ ያዳመጠ ፡ ያው ፡ በክብር ፡ ተገለጠ

የሰማው ፡ ከላይ ፡ ነው (፫x)
የሰማው ፡ ከላይ ፡ ነው (፫x)

አዝ:- ሰሞኑን ፡ ሰማሁ ፡ ክፉ ፡ ወሬ
በተወለድኩበት ፡ በአገሬ
ትንሹ ፡ ዮሴፍ ፡ በሕይወት ፡ አለ
አባትዬው ፡ ሰምቶ ፡ ጉድ ፡ አለ
እረ ፡ እኔ ፡ አልሞትኩም ፡ አለሁ
እረ ፡ እኔ ፡ አልሞትኩም (፫x)

ይሄ ፡ ነው ፡ ተነስ ፡ ቀባው ፡ የኔን ፡ ልብ ፡ ያሳረፈው (፪x)
ነብዩ ፡ ቀብቶት ፡ ወጣ ፡ ቅባቱ ፡ ነገር ፡ አመጣ
ከጐልያድ ፡ ጭንቅ፡ ያሳረፈውን ፡ መልሶ ፡ ጠላት ፡ ሆነዉ
የእግዚአብሔር ፡ ቃሉ ፡ አልፈረሰም ፡ ሳኦል ፡ ሞቶ ፡ ዳዊት ፡ ነገሠ

የሰማው ፡ ከላይ ፡ ነው (፫x)
የሰማው ፡ ከላይ ፡ ነው (፫x)

አዝ:- ሰሞኑን ፡ ሰማሁ ፡ ክፉ ፡ ወሬ
በተወለድኩበት ፡ በአገሬ
ትንሹ ፡ ዮሴፍ ፡ በሕይወት ፡ አለ
አባትዬው ፡ ሰምቶ ፡ ጉድ ፡ አለ
እረ ፡ እኔ ፡ አልሞትኩም ፡ አለሁ
እረ ፡ እኔ ፡ አልሞትኩም (፫x)

ስኬቴ ፡ ያስከፋቸው ፡ ውድቀቴ ፡ ደስ ፡ ያላቸው (፪x)
ላልሞተ ፡ ሰው ፡ አስለቅሶ ፡ በቁሜ ፡ አፈር ፡ አልብሰው
ልብ ፡ ሊስቅ ፡ እንደለመዱ ፡ ለታይታ ፡ ሙሾ ፡ ወረዱ
ከሰማይ ፡ በቃቹህ ፡ አለ ፡ ለዘሩት ፡ ዋጋ ፡ ከፈለ

የያዘኝ ፡ እጁ ፡ ነው (፫x)
የያዘኝ ፡ እጁ ፡ ነው (፫x)

አዝ:- ሰሞኑን ፡ ሰማሁ ፡ ክፉ ፡ ወሬ
በተወለድኩበት ፡ በአገሬ
ትንሹ ፡ ዮሴፍ ፡ በሕይወት ፡ አለ
አባትዬው ፡ ሰምቶ ፡ ጉድ ፡ አለ
እረ ፡ እኔ ፡ አልሞትኩም ፡ አለሁ
እረ ፡ እኔ ፡ አልሞትኩም (፫x)