From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
መገመት ፡ መብቱ ፡ ነው ፡ አያልፈውም ፡ ብሎ
እኔ ፡ ግን ፡ አልፋለሁ ፡ ገማቼ ፡ ቁጭ ፡ ብሎ
አውላ ፡ ????? ፡ ቢያነፋ ፡ መርከብ ፡ ቢሰበር
ቄሳር ፡ ስለኢየሱስ ፡ መስማቱ ፡ አይቀር
አዝ:- እዚሁ ፡ እንድትቀር ፡ መንገድህን ፡ የዘጋ (፪x) ፡ ወገቡ ፡ ተወጋ
መርዛማው ፡ እልፉኝት??? ፡ ትላንት ፡ የነደፈህ (፪x) ፡ ዛሬ ፡ ተራገፈ
የያዝከው ፡ ኢየሱስ ፡ ለሌላው ፡ ተረፈ
ለሌላ ፡ አለው ፡ መላ (፬x)
ማእበሉን ፡ አልሰማም ፡ ነው ፡ ያለኝን ፡ ትቼ ፡ የጠራኝን ፡ ትቼ
ሰይጣን ፡ ለምን ፡ ይሳቅ ፡ ውሃው ፡ ላይ ፡ ቀርቼ (፪x)
አላማ ፡ አለኝ ፡ ማእበሉ ፡ አያሰጥመኝ
አላማ ፡ አለኝ ፡ ማእበሉ ፡ አያስቀረኝ (፪x)
ሰባት ፡ እጥፍ ፡ አድርገው ፡ እሳት ፡ አነደዱ
ታላቁን ፡ መምህር ፡ ኢየሱስን ፡ ሊያስኪዱ
ለጣኦት ፡ ከምሰግድ ፡ ይብላኝ ፡ ይሄ ፡ እሳት
ስግደት ፡ የሚያምርብኝ ፡ ኢየሱሴ ፡ ፊት
አዝ:- እዚሁ ፡ እንድትቀር ፡ መንገድህን ፡ የዘጋ (፪x) ፡ ወገቡ ፡ ተወጋ
መርዛማው ፡ እልፉኝት??? ፡ ትላንት ፡ የነደፈህ (፪x) ፡ ዛሬ ፡ ተራገፈ
የያዝከው ፡ ኢየሱስ ፡ ለሌላው ፡ ተረፈ
ለሌላ ፡ አለው ፡ መላ (፬x)
ማእበሉን ፡ አልሰማም ፡ ነው ፡ ያለኝን ፡ ትቼ ፡ የጠራኝን ፡ ትቼ
ሰይጣን ፡ ለምን ፡ ይሳቅ ፡ ውሃው ፡ ላይ ፡ ቀርቼ (፪x)
አላማ ፡ አለኝ ፡ ማእበሉ ፡ አያሰጥመኝ
አላማ ፡ አለኝ ፡ ማእበሉ ፡ አያስቀረኝ (፬x)
|