እንደገና (Endegena) - ኢላሻ ፍቃዱ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኢላሻ ፍቃዱ
(Israel Fikadu)

Lyrics.jpg


(1)

1
(Endegena)

ዓ.ም. (Year): 2021
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኢላሻ ፍቃዱ ፡ አልበሞች
(Albums by Israel Fikadu)

አብዝቼውም ቻልከኝ
አልሰለቸህም
ትዕግስትህን ያሟጠጥሁኝ መስሎኝ
ለካ ልክ የለውም
ተስፋ መቁረጤ አላስቆመህም
ከፍቅር ዓላማህ
ስሠባበር ስትጠግን
አለቀ ስል ስትጀምር
ምስጋና
ለጸጋህ ክብር

እንደገና ረዳኸኝ
እንደገና አቆምከኝ
እንደገና ራራህልኝ
እንደገና አቆምከኝ

እንደገና /2x

የማይመጥነኝ ቦታ
ፈቅጄ ስገኝ
ፍቅርህን ካልቀመሱት ጋራ
ያሻኝን ስሆን
ያዋቂ አጥፊ
ደሜን አክፋፊ
ብለህ አልተውኸኝ
እየገፋሁህ ትቀርበኛለህ
በደሌን መች ትቆጥራለህ
ያለ ልክ ትወደኛለህ

እንደገና ረዳኸኝ
እንደገና አቆምኸኝ
እንደገና ራራህልኝ
እንደገና አቆምኸኝ

እንደገና / 2x