እንውጣ ፡ ለወንጌል (Enwuta Lewongel) - ሆሳዕና ፡ ቃለ ፡ ሕይወት ፡ ሐ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሆሳዕና ፡ ቃለ ፡ ሕይወት ፡ ሐ ፡ መዘምራን
(Hosana Kale Hiwot C Choir)

Lyrics.jpg


(1)

እንውጣ ፡ ለወንጌል
(Enewta Lewongel)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:32
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሆሳዕና ፡ ቃለ ፡ ሕይወት ፡ ሐ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Hosana Kale Hiwot C Choir)

ክቡር ፡ ቅርሳቸውን ፡ ቀዬያቸውን ፡ ትተው
ቁልቁል ፡ ወረዱ ፡ ማዕረጋቸውን ፡ ጥለው
ነፍስ ፡ አወራርደው ፡ ለወንጌል ፡ እውነት
ወስነው ፡ ወጡ ፡ ሞትን ፡ ለመሞት
መኖርያ ፡ ዘመድ ፡ ሃገር ፡ እያላቸው
ለወንጌል ፡ ብለው ፡ አውሬ ፡ በላቸው
እንደተረገሙ ፡ ሰው ፡ ቆጥሯቸው
ለሃገር ፡ ሁሉ ፡ ጦስ ፡ አረጓቸው

አዝ፦ ታሪኩን ፡ ሰምተን ፡ ዝም ፡ አይደል
እንውጣ ፡ ለወንጌል ፡ እንጋደል
ለምን ፡ እንተኛለን ፡ የእግዜአብሄር ፡ ሰዎች
ሲጨምር ፡ ቁጥራቸው ፡ የምድር ፡ ሙታኖች
ለእኛም ፡ ተሰብኮ ፡ ነው ፡ የመጣነው
አባቶቻችን ፡ ዋጋ ፡ ከፍለው
የአባቶቻችን ፡ አጥንት ፡ ይታዘበናል
ኧረ ፡ እያሱስ ፡ ምን ፡ ይለናል

ያለ ፡ ዳኛ ፡ ፍርድ ፡ ታርደው ፡ ተጣሉ
ክቡር ፡ ሰው ፡ ሲሆኑ ፡ ከእቃም ፡ ቀለሉ
ሰአትን ፡ ሳይመርጡ ፡ ያለመታከት
ሌሊቱን ፡ ከቀን ፡ የሚያገናኙ
ያለ ፡ እረፍት ፡ እንቅልፍ ፡ ከቀን ፡ እስከ ፡ ንጋት
በወህኒ ፡ ግርፋት ፡ የመከራው ፡ ስደት (፪x)

ረሃብ ፡ ዘመዳችው ፡ ጥማት ፡ ጓደኛቸው
ብርድና ፡ ውርጩ ፡ ውጭ ፡ አዳራቸው
የቀትሩ ፡ ፀሃይ ፡ የሀሩሩ ፡ ብዛት
ረዥሙ ፡ በረሃ ፡ የማይሻል ፡ ከሞት
አከሰላቸው ፡ መልካቸውን ፡ አጡ
ጤንነታቸውን ፡ ለወንጌል ፡ ተዉ (፪x)

አዝ፦ ታሪኩን ፡ ሰምተን ፡ ዝም ፡ አይደል
እንውጣ ፡ ለወንጌል ፡ እንጋደል
ለምን ፡ እንተኛለን ፡ የእግዜአብሄር ፡ ሰዎች
ሲጨምር ፡ ቁጥራቸው ፡ የምድር ፡ ሙታኖች
ለእኛም ፡ ተሰብኮ ፡ ነው ፡ የመጣነው
አባቶቻችን ፡ ዋጋ ፡ ከፍለው
የአባቶቻችን ፡ አጥንት ፡ ይታዘበናል
ኧረ ፡ እያሱስ ፡ ምን ፡ ይለናል

ለጌታ ፡ ቃል ፡ ብለው ፡ ከቤተሰባቸው
ከምወዱት ፡ ሃገር ፡ ከልጅ ፡ ከአባታቸው
ተለይተው ፡ ወጡ ፡ ጠፋ ፡ አድራሻቸው
ገደል ፡ ተራራ ፡ ስር ፡ ሆነ ፡ መኖርያቸው
ተባብረው ፡ ጠሏቸው ፡ ፍጥረታት ፡ ሁሉ
ቀባሪ ፡ ኣጡ ፡ በሜዳ ፡ ተጣሉ
ተሰነጠቁ ፡ ህይዎት ፡ እያላቸው
ያለፉት ፡ ሰማእታት ፡ አቤት ፡ ስቃያቸው

አዝ፦ ታሪኩን ፡ ሰምተን ፡ ዝም ፡ አይደል
እንውጣ ፡ ለወንጌል ፡ እንጋደል
ለምን ፡ እንተኛለን ፡ የእግዜአብሄር ፡ ሰዎች
ሲጨምር ፡ ቁጥራቸው ፡ የምድር ፡ ሙታኖች
ለእኛም ፡ ተሰብኮ ፡ ነው ፡ የመጣነው
አባቶቻችን ፡ ዋጋ ፡ ከፍለው
የአባቶቻችን ፡ አጥንት ፡ ይታዘበናል
ኧረ ፡ እያሱስ ፡ ምን ፡ ይለናል