From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ባልጠፋ ፡ ሰው ፡ በእኔ ፡ አካል ፡ ውስጥ ፡ ገባህ
መኖርያ ፡ ለክብርህ ፡ ሰራህ ፡ ኣበጃህ
ስትገባ ፡ በውስጤ ፡ ሰው ፡ ሰው ፡ ሸተትኩኝ
ከሙቱ ፡ ከእኔ ፡ ሕይወት ፡ ሰላም ፡ ወጣኝ
ኃይሉ ፡ የሰው ፡ ቢሆን ፡ የአምላካችን ፡ የእግዚአብሔር
ከእኛ ፡ መካከል ፡ እነማን ፡ እንጠራ ፡ ነበር
እንዴት ፡ ይሆናል ፡ የእናንተን ፡ በእርግጥ ፡ ባላውቅም
በእኔ ፡ እይታ ፡ ግን ፡ ለአምላኬ ፡ መንግስት ፡ አይታሰብም
ምስኪን ፡ ምናምንቴ ፡ ለቁም ፡ ነገር ፡ ማልሆን
ፀጋ ፡ ቢስ ፡ ሌባ ፡ ሸክላ ፡ ነኝ ፡ ምሰበር
ከጠላቴ ፡ መቅሰፍት ፡ ስሸሽ ፡ አየኝና
ከሞት ፡ አተረፈኝ ፡ በውስጤ ፡ ገባና
አዝ፦ ባልጠፋ ፡ ሰው ፡ በእኔ ፡ አካል ፡ ውስጥ ፡ ገባህ
መኖርያ ፡ ለክብርህ ፡ ሰራህ ፡ ኣበጃህ
ስትገባ ፡ በውስጤ ፡ ሰው ፡ ሰው ፡ ሸተትኩኝ
ከሙቱ ፡ ከእኔ ፡ ሕይወት ፡ ሰላም ፡ ወጣኝ
የሰው ፡ ሰው ፡ የተባሉ ፡ በጣም ፡ ባላቸው ፡ የከበሩ
እኔን ፡ ለምን ፡ ጠራኝ ፡ በምን ፡ ምክንያት ፡ እነሱ ፡ ቀሩ
እኔጃ ፡ ምክንያቱ ፡ በውል ፡ በቅጥ ፡ ባይገባኝም
እኔን ፡ ያስወደደው ፡ ፍቅሩ ፡ ነው ፡ ይህንን ፡ አልክድም
ፍቅር ፡ ሀይለኛ ፡ ነው ፡ ኃጢአት ፡ ያስሻረው
ይመስገን ፡ እየሱስ ፡ ህይዎቴ ፡ ከዚያ ፡ ነው
አዝ፦ ባልጠፋ ፡ ሰው ፡ በእኔ ፡ አካል ፡ ውስጥ ፡ ገባህ
መኖርያ ፡ ለክብርህ ፡ ሰራህ ፡ ኣበጃህ
ስትገባ ፡ በውስጤ ፡ ሰው ፡ ሰው ፡ ሸተትኩኝ
ከሙቱ ፡ ከእኔ ፡ ሕይወት ፡ ሰላም ፡ ወጣኝ
አምላኬ ፡ እንዲገባ ፡ ውስጤን ፡ ለእሱ ፡ አላስዋብኩለት
መንገድ ፡ አላበጀው ፡ ቤቴንም ፡ አላጸደሁለት
በጠጠር ፡ በእሾህ ፡ ተራምዶ ፡ ነው ፡ ቤቴ ፡ የመጣው
ገረመኝ ፡ ፍቅሩ ፡ የታላቁ ፡ ንጉስ ፡ ትህትና
ሰባራ ፡ ቀዳዳውን ፡ ጠራርጎ ፡ ገባ
እረፍትን ፡ ሰጣኝ ፡ ሰላሜን ፡ አበዛ
|