ይወጣል (Yewetal) - ሂሩት ፡ ሞገስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሂሩት ፡ ሞገስ
(Hirut Moges)

Hirut Moges 2.png


(2)

ላልተጠራሁለት ፡ እኔ ፡ አልኖርም
(Lalteterahulet Alnorem)

ዓ.ም. (Year): ፲፱፻፺፱ (2006)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሂሩት ፡ ሞገስ ፡ አልበሞች
(Albums by Hirut Moges)

ከእግዚኣብሔር ፡ ጋር ፡ የሆነውን ፡ ሰው ፡ ማን ፡ ይረታል? ኦሆሆ
ማን ፡ ይረታል? ኦሆሆ ፡ ማን ፡ ይረታል? ኦሆሆ
በድል ፡ ወጥቶ ፡ በድል ፡ ይገባል ፡ ያሸንፋል ፡ ኦሆሆ
ያሸንፋል ፡ ኦሆሆ ፡ ያሸንፋል ፡ ኦሆሆ

ጌታ ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ የሆነ ፡ ሰው ፡ ኦሆሆ
ይወጣል ፡ ይወርሳል ፡ ያስወርሳል (፬x) ፡ ኦሆሆ

ሁለቱ ፡ ብቻ ፡ ተለይተው ፡ ከአሥሩ
የዕምነት ፡ ቃል ፡ በድፍረት ፡ ሲናገሩ
መውረስ ፡ ብቻ ፡ ነበር ፡ የሚታያቸው
እንውጣና ፡ እንውረስ ፡ ነው ፡ ቋንቋቸው
እንዲሁ ፡ እንዳሉት ፡ ሆነላቸው
እግዚኣብሔርም ፡ ተስፋቸውን ፡ አስወረሳቸው

እንደ ፡ ካሌብ ፡ ኦሆሆ ፡ እንደ ፡ ኢያሱ
እኔንም ፡ አርገኝ ፡ ጌታዬ ፡ እንደነርሱ

የእግዚኣብሔር ፡ ሰው ፡ ሽንፈትን ፡ አያወራም
በሚሰማው ፡ በሚታየው ፡ አይፈራም
የፊቱን ፡ ሊይዝ ፡ የኃላውን ፡ ይረሳል
ቃል ፡ ስላለው ፡ የረገጠውን ፡ ይወርሳል

እርሱማ ፡ ከሰው ፡ ሁሉ ፡ ይለያል
እግዚኣብሔር ፡ ያየውን ፡ ብቻ ፡ ያያል
ፊት ፡ ለፊት ፡ ገጥሞ ፡ ኦሆሆ ፡ ከጠላቱ
ባለድል ፡ እርሱ ፡ ይሆናል ፡ በጦርነቱ

የእግዚኣብሔር ፡ ሰው ፡ ሲናገር ፡ ያስተውላል
መልካም ፡ ነገር ፡ አድሮ ፡ ሲያስብ ፡ አድሮ ፡ ይውላል
ዋዘኞችን ፡ ፡ ፌዘኞችን ፡ ይጠላል
ለያዘው ፡ ዕውነት ፡ እስከ ፡ ሞት ፡ ይጨክናል
እሱማ ፡ ነው ፡ ፡ የአስተዋይ ፡ ባልንጀራ
ዕውነት ፡ ብቻ ፡ በአፍ ፡ የሚያወራ
ለራዕዩ ፡ ዋጋ ፡ ይከፍላል ፡ ይለፋል
በዘመኑም ፡ ቁምነገር ፡ ሠርቶ ፡ ያልፋል
ምሣሌ ፡ ሆኖ ፡ ኦሆሆ ፡ ለሰው ፡ ሁሉ
በድል ፡ ይወጣል ፡ ይገባል ፡ ታምኖ ፡ በቃሉ