ያልተባለልህ (Yaltebaleleh) - ሂሩት ፡ ሞገስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሂሩት ፡ ሞገስ
(Hirut Moges)

Hirut Moges 2.png


(2)

ላልተጠራሁለት ፡ እኔ ፡ አልኖርም
(Lalteterahulet Alnorem)

ዓ.ም. (Year): ፲፱፻፺፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሂሩት ፡ ሞገስ ፡ አልበሞች
(Albums by Hirut Moges)


ብዙዎች ፡ ብዙ ፡ ብለውሃል (፬x)
እግዚኣብሔር ፡ ከተባልከው ፡ ሁሉ ፡ በልጠሃል
አምልኮና ፡ ስግደት ፡ ዛሬም ፡ ይገባሃል
አምልኮና ፡ ስግደት ፡ ሁሌም ፡ ይገባሃል

ያልተባለልህ (፬x)
ገና ፡ ገና ፡ ብዙ ፡ አለልህ

ያልሰማነው ፡ ገና ፡ ያላየነው ፡ ገና ፡ ያላወቅነው ፡ ገና (፫x)
ጌታ ፡ ሆይ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ አለና
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ አለና
አምላክ ፡ ሆይ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ አለና
አባት ፡ ሆይ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ አለና

ያልተባለልህ (፬x)
ገና ፡ ገና ፡ ብዙ ፡ አለልህ

ዕውቀትህ ፡ ከአዋቂዎች ፡ የበላይ ፡ ነው
ጥበብህ ፡ ከጠቢባን ፡ በላይ ፡ ነው

ሥልጣንህ ፡ ከሥልጣናትም ፡ በላይ ፡ ነው
ኃይልህም ፡ ከሃይላት ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ነውግ
የእኛ ፡ ጌታ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ
አቤቱ ፡ የእኛ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ

እግዚኣብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ አና ፡ ያላወቅነው (፪x)
ካመለክንህም ፡ በላይ ፡ ካከበርንህም ፡ በላይ
ካደነቅንህም ፡ በላይ (፫x)

ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ነህና ፡ የበላይ
እግዚኣብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው
እኛ ፡ ያላወቅነው (፬x)