ውዴ ፡ ሆይ (Wedie Hoy) - ሂሩት ፡ ሞገስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሂሩት ፡ ሞገስ
(Hirut Moges)

Hirut Moges 2.png


(2)

ላልተጠራሁለት ፡ እኔ ፡ አልኖርም
(Lalteterahulet Alnorem)

ዓ.ም. (Year): ፲፱፻፺፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሂሩት ፡ ሞገስ ፡ አልበሞች
(Albums by Hirut Moges)


ትንሳኤ ፡ ታውጆልኝ
ሞቴ ፡ በሕይወት ፡ ተሽሮልኝ
ከአንተ ፡ ጋር ፡ ተወዳጅቼ
እዘምራለሁ ፡ ተፈትቼ

በመስቀል ፡ ጣር ፡ ወልደኸኝ
የአንተ ፡ የግል ፡ አደረግኸኝ
በቤትህ ፡ ውስጥ ፡ አሳደግኸኝ
ልጅህ ፡ ሆንኩኝ ፡ አባት ፡ ሆንኸኝ

ውዴ ፡ ሆይ (፰x)
አንተ ፡ የእኔ ፡ ነህ ፡ እኔም ፡ የአንተ ፡ እኮ ፡ ነኝ (፬x)

እኔ ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ አውቃለሁ
ይህም ፡ እውነት ፡ ነው ፡ አምናለሁ
ውዴ ፡ አላማህ ፡ በእኔ ፡ ላይ
ፍቅር ፡ ነው ፡ ከምንም ፡ በላይ

ነፍሴ ፡ እጅግ ፡ ወዳሃለች
ሌት ፡ ተቀን ፡ ውዴ ፡ ትላለች
ናፍቆቷ ፡ ነህ ፡ የዘወትር
ተማርካለች ፡ በአንተ ፡ ፍቅር

ከአንተ ፡ ጋር ፡ ጉዳይ ፡ አለኝ
ሰውማ ፡ ምንም ፡ ይበለኝ
አንተ ፡ ነህ ፡ ሚስጢረኛዬ
የበረሃው ፡ ጓደኛዬ

በፍቅርህ ፡ ተይዣለሁ
ሳላይህ ፡ እንዴት ፡ እውላለሁ
ዛሬ ፡ ልፈልግ ፡ ፊትህን
ተናግረህ ፡ ልስማ ፡ ድምጽህን