ተመስገን (Temesgen) - ሂሩት ፡ ሞገስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሂሩት ፡ ሞገስ
(Hirut Moges)

Hirut Moges 2.png


(2)

ላልተጠራሁለት ፡ እኔ ፡ አልኖርም
(Lalteterahulet Alnorem)

ዓ.ም. (Year): ፲፱፻፺፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሂሩት ፡ ሞገስ ፡ አልበሞች
(Albums by Hirut Moges)

ያደረግኸውን ፡ ሁሉ ፡ ሥራህን ፡ እያየሁ
እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ (፪x)
ላመስግን ፡ እንጂ ፡ አንተን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ከልቤ
ቅኔ ፡ እየተቀኘሁ (፪x)

ተመስገን ፡ ልበልህ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ (፪x)
ተባረክ ፡ ልበልህ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ (፪x)
ተወደስ ፡ ልበልህ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ (፪x)

ዛሬም ፡ ልበልህ ፡ ተመስገን
ነገም ፡ ልበልህ ፡ ተመስገን
ሁሌም ፡ ልበልህ ፡ አምላኬ ፡ ተመስገን

ጌታ ፡ ሆይ ፡ እድሜን ፡ መቁጠር ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ አውቃለሁ
በዚህ ፡ እደነቃለሁ (፪x)
ምህረትህ ፡ ለኔም ፡ በዝቶ ፡ ዛሬን ፡ አይቻለሁ
ላመልክህ ፡ ችያለሁ ፡ ላከብርህ ፡ ችያለሁ

አምላኬ ፡ አንተን ፡ ይዤ ፡ ትልቅ ፡ ሰው ፡ ተባልኩኝ
ባንተ ፡ ተከበርኩኝ (፪x)
ያልነበረኝን ፡ ሹመት ፡ ማዕረግ ፡ አግኝቻለሁ
እኔም ፡ ወግ ፡ አየሁኝ (፪x)

ጥሩ ፡ ስም ፡ ሰጥተኸኛል ፡ መልካም ፡ ሰው ፡ አርገኸኛል
እግዚኣብሔር ፡ ውለታ ፡ ውለህልኛል
ኦ ፡ ምስጋናዬን ፡ ላብዛብህ (፫x)
አሜን ፡ ምስጋናዬ ፡ ይብዛልህ (፫x)

ጥጋቤነህ ፡ ኩራቴ ፡ ነህ ፡ ትምክህቴ ፡ ነህ
ልጠግብም ፡ ባመልክህ
ኢየሱሴ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ ልበልህ
ተባረክ ፡ ተወደስ ፡ ክበር ፡ ከፍ ፡ በል