ላልተጠራሁለት ፡ እኔ ፡ አልኖርም (Lalteterahulet Enie Alnorem) - ሂሩት ፡ ሞገስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሂሩት ፡ ሞገስ
(Hirut Moges)

Hirut Moges 2.png


(2)

ላልተጠራሁለት ፡ አልኖርም
(Lalteterahulet Alnorem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሂሩት ፡ ሞገስ ፡ አልበሞች
(Albums by Hirut Moges)

አምላኬን ፡ ከልብ ፡ ኦሆሆ ፡ አመልካለሁ
ልዘምርለት ፡ ኦሆሆ ፡ ተለይቻለሁ
አከብረዋለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ ዛሬም ፡ በደስታ
ሥራዬ ፡ ሆኖአል ፡ ኦሆሆ ፡ መኖር ፡ ለጌታ

ያዘምረኛል ፡ ቅባቱ ፡ ያዘምረኛል
ያዘምረኛል ፡ ምሕረቱ ፡ ያዘምረኛል
ያዘምረኛል ፡ እሳቱ ፡ ያዘምረኛል

እኔን ፡ ጌታ ፡ እኔን ፡ ኢየሱስ ፡ አመልክህ ፡ ዘንድ ፡ ጠርተኸኛል
አከብርህ ፡ ዘንድ ፡ መርጠኸኛል ፡ አመልክህ ፡ ዘንድ ፡ ጠርተኸኛል

እኔም ፡ አንተ ፡ ኦሆሆ ፡ መድሃኒቴን ፡ አሀሀ
መመኪያዬ ፡ ኦሆሆ ፡ ማለፊያዬም ፡ አሀሀ
በሙሉ ፡ ሃይሌ ፡ ኦሆሆ ፡ በአዳዲስ ፡ ዕቅዴ ፡ አሃሃ
አመልክሃለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ አከብርሃለሁ ፡ ኦሆሆ
ሥራዬ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ በቃ (፬x)

እኔማ ፡ ለሃሜት ፡ ጊዜ ፡ የለኝም
በማንም ፡ ለመፍረድ ፡ ጌታ ፡ አልጠራኝም
የታዘዝኩትን ፡ ቁምነገር ፡ ልሰራ ፡ ጊዜ ፡ አልበቃኝም ፡ እኔ
ፅድቅን ፡ አላወራም ፡ ለተንኮል ፡ ለአመጽ ፡ ለክፋት

አዝ፦ አልተጠራሁም ፡ ለወሬ ፡ አልተጠራሁም ፡ ለሃሜት
አልተጠራሁም ፡ ለትችት ፡ አልተጠራሁም
ላልተጠራሁለት ፡ እኔ ፡ አልኖርም
የጠራኝን ፡ ጌታ ፡ አላሳፍርም

ታማኝ ፡ አርጎ ፡ ቆጥሮ ፡ በቤቱ፡ሲሾመኝ
ጌታዬ ፡ ለራሱ ፡ ለይቶ ፡ ሲያቆመኝ
እኔስ ፡ ለምን ፡ ልሂድ ፡ ወደ ፡ ውርደት ፡ ስፍራ
ወደተውኳት ፡ አለም ፡ ሃጥያት ፡ ልሰራ

አዝ፦ አልተጠራሁም ፡ ለአለም ፡ አልተጠራሁም ፡ ለሀጥያት
ለውሽት ፡ ለስርቆት ፡ ለዝሙት
አልተጠራሁም ፡ ለርኩሰት ፡ አልተጠራሁም
ላልተጠራሁለት ፡ አልኖርም ፡ የጠራኝን ፡ ጌታ ፡ አላሳፍርም

ማን ፡ እንደሆንኩኝ ፡ እኔ ፡ እራሴን ፡ አውቃለሁ
እግዚኣብሔር ፡ ሲያከብረኝ ፡ እንዴት ፡ እቀላለሁ
ለትልቅ ፡ አላማ ፡ ጌታ ፡ እኔን ፡ መርጦኛል
ደግሞም ፡ ለሰማዩም ፡ መንግስት ፡ አጭቶኛል

አዝ፦ አልተጠራሁም ፡ ለጥፋት ፡ አልተጠራሁም
ለመቅሰፍት ፡ ለሽንፈት ፡ ለውርደት ፡ ለውድቀት
አልተጠራሁም ፡ ለርግማን ፡ አልተጠራሁም
ላልተጠራሁለት ፡ እኔ ፡ አልኖርም ፡ የጠራኝን ፡ ጌታ ፡ አላሳፍርም