እሮጣለሁ (Erotalehu) - ሂሩት ፡ ሞገስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሂሩት ፡ ሞገስ
(Hirut Moges)

Hirut Moges 2.png


(2)

ላልተጠራሁለት ፡ እኔ ፡ አልኖርም
(Lalteterahulet Alnorem)

ዓ.ም. (Year): ፲፱፻፺፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሂሩት ፡ ሞገስ ፡ አልበሞች
(Albums by Hirut Moges)


ማዳኑን ፡ አይቻለሁ ፡ ምስክሩ ፡ ሆኛለሁ
ሥራውን ፡ አወራለሁ ፡ ጌታዬን ፡ አከብራለሁ

ከጌታ ፡ የተነሳ ፡ ነው ፡ በህይወት ፡ የምኖረው
ከኢየሱስ ፡ የተነሳ ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ የምዘምረው
ምህረቱ ፡ ቸርነቱ ፡ ለአኔ ፡ በዝቶልኝ ፡ ነው

የትናንቱን ፡ እየረሳሁ ፡ የዛሬውን ፡ ልጨብጥ
ወደፊት ፡ እዘረጋለሁ ፡ በአዲስ ፡ መገለጥ
ካየሁት ፡ ወደሚበልጠው ፡ ክብር ፡ እሮጣለሁ
 ካወቅሁት ፡ በላይ ፡ ለማወቅ ፡ እገሰግሳለሁ
 
እሮጣለሁ ፡ እስከመጨረሻ (፪x)
ይህ ፡ ነውና ፡ የእኔ ፡ ድርሻ
እጋደላለሁኝ ፡ መልካም ፡ ገድል
ከእጁ ፡ ለመውሰድ ፡ የፅድቅ ፡ አክሊል
 
የእውነትን ፡ ቃል ፡ በቅንነት ፡ እየተናገርኩኝ
 የምሥራቹን ፡ ለፍጥረት ፡ እያበሰርኩኝ
የማላሳፍር ፡ ሠራተኛ ፡ ሆኜ ፡ በዚች ፡ ምድር
እተጋለሁኝ ፡ እሩጫዬን ፡ ልፈጽም ፡ ዘወትር

መልካሙን ፡ ገድል ፡ ተጋድዬ ፡ ሩጫዬን ፡ ስጨርስ
ሐይማኖቴንም ፡ ጠብቄ ፡ ወደ ፡ ሀገሬ ፡ ስደርስ
ጻድቅ ፡ ፈራጅ ፡ የሆነው ፡ ጌታ ፡ ያኔ ፡ ይሸልመኛል
የተዘጋጀልኝን ፡ አክሊል ፡ ያስረክበኛል

መዳኔን ፡ አይቻለሁ ፡ ምስክሩ ፡ ሆኛለሁ
ሥራውን ፡ አወራለሁ ፡ ጌታዬን ፡ አከብራለሁ