From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
እግዚኣብሔርን ፡ መፍራት ፡ ጥበብ ፡ ነው ፡ የጥበብ ፡ ሁሉ ፡ መጀመሪያ
ከሃጢያት ፡ መራቅ ፡ ማስተዋል ፡ ነው ፡ ሃሌሉያ
እግዚኣብሔርን ፡ የሚፈራ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ደስታ ፡ ያያል
በምድር ፡ ላይ ፡ እድሜው ፡ ይረዝማል ፡ በበረከት ፡ ይኖራል
አይራብም ፡ እርሱ ፡ ከቶ ፡ እግዚኣብሔር ፡ ጥጋብ ፡ ይሆነዋል
በመከራ ፡ ዘመን ፡ አይሰጋም ፡ ጌታ ፡ በድል ፡ ያሳልፈዋል
እንዴት ፡ የእግዚኣብሔር ፡ ፊት ፡ ሃጥያት ፡ እሰራለሁኝ ፡ ብሎ
እግዚኣብሔርን ፡ ፈርቶ ፡ ዮሴፍ ፡ ሸሸ ፡ ከሃጥያት ፡ ኮብልሎ
እየጨመረ ፡ ቢሄድም ፡ ፈተናው ፡ ቢሆን ፡ ያየለ
አምላኩ ፡ ሲያስበው ፡ ከበር ፡ መች ፡ ቀረ ፡ እንደተጣለ
እግዚኣብሔርን ፡ በመፍራቱ ፡ የገባ ፡ ከእግዚኣብሔር ፡ እይታ
በምድር ፡ ላይ ፡ ቅን ፡ ሰው ፡ የተባለ ፡ ለጠላቱ ፡ ያልተረታ
እዮብም ፡ ታስቦአል ፡ በጊዜው ፡ በመከራው ፡ ሁሉ ፡ ታግሶ
ከሳሹን ፡ አሳፈረለት ፡ ጌታ ፡ ምርኮውን ፡ መልሶ
የሰው ፡ ልጅ ፡ ጥበብን ፡ ለማግኘት ፡ በዘመኑ ፡ ሁሉ ፡ ይደክማል
ጥበብ ፡ ግን ፡ እግዚኣብሔር ፡ መሆኑን ፡ ያወቀ ፡ ከርሱ ፡ ጋር ፡ ይስማማል
ዘመኑን ፡ በተድላ ፡ ሊጨርስ ፡ የሚፈልግ ፡ እግዚኣብሔርን ፡ ይፍራ
በመውጣት ፡ በመግባቱ ፡ ሁሉ ፡ ያክብረው ፡ በየትኛውም ፡ ስፍራ
እንደቀደሙቱ ፡ ሐዋሪያት ፡ ላንተ ፡ እንደተሰጡ ፡ ነቢያት
እኔንም ፡ ቁምነገረኛ ፡ ሰው ፡ ለማድረግ ፡ ሕይወቴን ፡ ቀደሰው
ጌታዬ ፡ በሰጠኸኝ ፡ መክሊት ፡ ነግጄበት ፡ ቀንና ፡ ሌሊት
ለመጨረሻው ፡ ቀን ፡ ሽልማት ፡ በድል ፡ አዘጋጀኝ ፡ የኔ ፡ አባት
ታማኝ ፡ ባሪያ ፡ አድርገኝ ፡ ጌታዬ
እንዲፈጸም ፡ ባንተ ፡ ደስታዬ
ታማኝ ፡ ባሪያ ፡ አድርገኝ ፡ ኢየሱሴ ፡ ይህን ፡ ትሻለች ፡ ካንተ ፡ ነፍሴ
እንደ ፡ ዳዊት ፡ በኔ ፡ ሕይወት ፡ ሰልፉን ፡ ቢያበዛብኝም ፡ ጠላት
መንገዴን ፡ ለአንተ ፡ አደራ ፡ ብዬ ፡ እንድጛዝ ፡ እርዳኝ ፡ አባብዬ
ፍጹም ፡ ሳልታጣ ፡ ከፊትሕ ፡ ይፈጸም ፡ በሕይወቴ ፡ ሃሳብህ
አምላኬ ፡ በዚህ ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ እርዳኝ ፡ ለቤትህ ፡ ፡ እንድታመን
|