From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ደስ ፡ ይበላችሁ (፪x)
ደግሜ ፡ እላለሁ ፡ በጌታ
ሁልጊዜ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
በመጠራታችሁ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
ተስፋ ፡ ስላላችሁ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
በአሸናፊው ፡ ጌታችሁ ፡ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
እጅግ ፡ ሃሤት ፡ አድርጉ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
አዝ፦ ደስ ፡ ይበላችሁ (፪x)
ደግሜ ፡ እላለሁ ፡ በጌታ
ሁልጊዜ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
በዚህ ፡ በአንድነታችሁ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክብራችሁ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
ጠላት ፡ ቢነሣባችሁ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
አይተኛም ፡ ጠባቂያችሁ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
አዝ፦ ደስ ፡ ይበላችሁ (፪x)
ደግሜ ፡ እላለሁ ፡ በጌታ
ሁልጊዜ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
ምንም ፡ ነገር ፡ ብታጡም ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
ደግሞም ፡ ብታገኙም ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
ጌታ ፡ ይክበርባችሁ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
አዝ፦ ደስ ፡ ይበላችሁ (፪x)
ደግሜ ፡ እላለሁ ፡ በጌታ
ሁልጊዜ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
ጌታ ፡ ነው ፡ ሰላማችሁ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
በ ፡ አንዳች ፡ አትጨነቁ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
ሁሉን ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ጣሉ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ኢኤልሻዳዩ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
ስላለፈው ፡ ነገር ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
ከፊት ፡ ስለሚመጣው ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
በረጅሙ ፡ ጉዞ ፡ አችሁ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መሪ ፡ ያችሁ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
አዝ፦ ደስ ፡ ይበላችሁ (፪x)
ደግሜ ፡ እላለሁ ፡ በጌታ
ሁልጊዜ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
|