አዋጅ (Awaj) - ሂሩት ፡ ሞገስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሂሩት ፡ ሞገስ
(Hirut Moges)

Hirut Moges 2.png


(2)

ላልተጠራሁለት ፡ እኔ ፡ አልኖርም
(Lalteterahulet Alnorem)

ዓ.ም. (Year): ፲፱፻፺፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሂሩት ፡ ሞገስ ፡ አልበሞች
(Albums by Hirut Moges)

ዘመኑ ፡ ክፉ ፡ ነው ፡ ክፉ ፡ ነው ፡ እጅግ ፡ ክፉ ፡ ነው
ደግሞ ፡ ኪሣራው ፡ ያመዝናል ፡ ከትርፉ
የዚህ ፡ ዘመን ፡ ማለፊያ ፡ መሸጋገሪያ ፡ ድልድይ
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ የሚያሳርፍ ፡ ከሥቃይ

አዋጅ ፡ አዋጅ ፡ ያልሰማችሁ ፡ ስሙ
ኢየሱስ ፡ ያድናል (፮x)

የመዳን ፡ መንገዱ ፡ አንዱ ፡ ነው ፡ እርሱም ፡ ኢየሱስ
ሌላ ፡ መንገድ ፡ የለም ፡ ወደ ፡ ዓብ ፡ የሚያደርስ
በልጁ ፡ ያመነ ፡ አይፈረድበትም
በሕይወት ፡ ይኖራል ፡ ለዘለኣለም ፡ አይሞትም
መድሃኒት ፡ ለታጣው ፡ ለዓለም ፡ አይሞትም

መድሃኒት ፡ ለታጣው ፡ ለዓለም ፡ ሁሉ ፡ በሽታ
መፍትሔ ፡ የሚሆን ፡ እንቆቅልሽ ፡ የሚፈታ
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ሕይወትን ፡ የሚያለማ

ጆሮ ፡ ያለው ፡ ቢኖር ፡ ይህን ፡ ዕውነት ፡ ይስማ
ከሰማየ ፡ ሰማያት ፡ ፃድቁ ፡ አምላክ ፡ ወርዶ
በምድር ፡ ተዋረደ ፡ በኛ ፡ ፍቅር ፡ ተገዶ
ሞትን ፡ ድል ፡ ያረገው ፡ የትንሣኤው ፡ ባለቤት
ጥሪውን ፡ ያስተጋባ ፡ ለሁሉም ፡ በያለበት

መሃሪ ፡ ነው (፪x) ፡ ጌታ ፡ መሃሪ ፡ ነው
የማታውቁ ፡ ዛሬ ፡ እወቁ ፡ ኢየሱስ ፡ ይቅር ፡ ባይ ፡ ነው

የምሕረት ፡ ቃል ፡ ያለህ ፡ የምሕረት ፡ ቃል
የሕይወት ፡ ቃል ፡ ያለህ ፡ የሕይወት ፡ ቃል
ጌታ ፡ ሆይ ፡ እንዳንተ ፡ ማን ፡ ይታደጋል?
የፍቅር ፡ ቃል ፡ ያለህ ፡ የፍቅር ፡ ቃል
የምክር ፡ ቃል ፡ ያለህ ፡ የምክር ፡ ቃል
ጌታ ፡ ሆይ ፡ እንዳንተ ፡ ማን ፡ ያሳርፋል?

በርሱ ፡ ለታመነው ፡ ላመነው ፡ ጌታ ፡ ታማኝ ፡ ነው (፫x)
እርሱ ፡ ታማኝ ፡ ነው (፬x)

መሃሪ ፡ ነው (፪x) ፡ ጌታ ፡ ይቅር ፡ ባይ ፡ ነው
የማታውቁ ፡ ዛሬ ፡ እወቁ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒት ፡ ነው