አሻፈረኝ (Ashaferegn) - ሂሩት ፡ ሞገስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሂሩት ፡ ሞገስ
(Hirut Moges)

Hirut Moges 2.png


(2)

ላልተጠራሁለት ፡ እኔ ፡ አልኖርም
(Lalteterahulet Alnorem)

ዓ.ም. (Year): ፲፱፻፺፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሂሩት ፡ ሞገስ ፡ አልበሞች
(Albums by Hirut Moges)


ኢየሱስ ፡ ሲጠራኝ ፡ እርሱን ፡ ተከተልኩኝ (፪x)
በጣም ፡ ረጅም ፡ መንገድ ፡ ተጉዤ ፡ መጣሁኝ (፪x)

ከእንግዲህ ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ ዞር ፡ ብዬ ፡ አላይም
የመጣ ፡ ይምጣ ፡ እንጂ ፡ ከርሱ ፡ አልለይም
አሻፈረኝ ፡ አሃ ፡ ወደኋላ ፡ አልመለስም

ወስኛለሁ ፡ አንዴ ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ አልለየውም
የረሳሁት ፡ ነገር ፡ ከኋላ ፡ ቢኖርም
ይቅርብኝ ፡ ብያለሁ ፡ ከኢየሱስ ፡ አይበልጥም

ለእኔ ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ማን ፡ ይሆንልኛል (፪x)
በዓለም ፡ ካለው ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ በልጦብኛል (፪x)

እኔ ፡ መርጨዋለሁ ፡ ምንም ፡ ሳላቅማማ
ዛሬ ፡ እፎክራለሁ ፡ ጠላት ፡ እየሰማ

የመኖር ፡ ትርጉሙ ፡ ፍጹም ፡ ግራ ፡ ገብቶኝ (፪x)
ሌት ፡ ተቀን ፡ ስጨነቅ ፡ የማደርገው ፡ ጠፍቶኝ (፪x)
ከእለታት ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ብቅ ፡ አለልኝ
ጨልሞ ፡ የነበረው ፡ ተስፋዬም ፡ በራልኝ

እንደቀድሞ ፡ እንደኔ ፡ ግራ ፡ የተጋባችሁ
ነግቶ ፡ ሳለ ፡ ቀኑ ፡ የጨለመባችሁ
ወደ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ እኔ ፡ ልጋብዛችሁ
እና ፡ በእርሱ ፡ ብርሃን ፡ ብርሃን ፡ ታያላችሁ

እስከዛሬ ፡ ጌታ ፡ ሰርተሃል
ከንግዲህስ ፡ ቢሆን ፡ ምን ፡ ይሳንሃል

እኔ ፡ በአንተ ፡ ተስፋ ፡ አልቆርጥም
በጠላቴ ፡ ዛቻ ፡ ከቶ ፡ አልናወጥም
የኤርትራን ፡ ባህር ፡ በክንድህ ፡ ከፍለሃል
ፈረሱን ፡ ፈረሰኛውን ፡ በባሕር ፡ ጥለሃል

ዛሬም ፡ በእኛ ፡ ዘመን ፡ ክንድህ ፡ ስላልዛለ
የጠላትን ፡ ስራ ፡ ታፈራርሳለህ
እስከዛሬ ፡ ጌታ ፡ ሰርተሃል