አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ (Ante Eko Neh) - ሂሩት ፡ ሞገስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሂሩት ፡ ሞገስ
(Hirut Moges)

Hirut Moges 2.png


(2)

ላልተጠራሁለት ፡ እኔ ፡ አልኖርም
(Lalteterahulet Alnorem)

ዓ.ም. (Year): ፲፱፻፺፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሂሩት ፡ ሞገስ ፡ አልበሞች
(Albums by Hirut Moges)

ወልዶ ፡ አይጥልም ፡ ጌታ ፡ ያሳድጋል
አሳድጎም ፡ ለማዕረግ ፡ ለወግም ፡ ያበቃል (፪x)

አይቻለሁ ፡ በዓይኔ ፡ ጌታን ፡ በዘመኔ
አይቻለሁ ፡ በዓይኔ ፡ ጥበቃውን ፡ በኔ
አይቻለሁ ፡ በዓይኔ ፡ ጌታን ፡ በዘመኔ
አይቻለሁ ፡ በዓይኔ ፡ አባት ፡ ሆኖኝ ፡ ለኔ
አይቻለሁ ፡ በዓይኔ ፡ ጌታን ፡ በዘመኔ
አይቻለሁ ፡ በዓይኔ ፡ ታማኝ ፡ ሆኖ ፡ ለኔ

አስቸጋሪ ፡ የሆነውን ፡ ዓመሌን ፡ ችለሃል
ከማንም ፡ ሰው ፡ ይልቅ ፡ ለኔ ፡ አንተ ፡ ተመችተኸኛል
አባቴ ፡ ሆይ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አለ
በፍቅር ፡ የሚያባክን ፡ ሁሉንም ፡ አይቻለሁ

አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ሰብሳቢዬ ፡ ኢየሱስዬ ፡ አሳዳጊዬ ፡ ኢየሱስዬ (፬x)
መካሪዬ ፡ ኢየሱስዬ ፡ መጠሪያዬ ፡ ኢየሱስዬ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ
መካሪዬ ፡ ኢየሱስዬ ፡ መጠሪያዬ ፡ ኢየሱስዬ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ

ያለ ፡ አማካሪ ፡ ብቻህን ፡ ታምራት ፡ ታደርጋለህ
ሃጥያተኛን ፡ ቀድሰህ ፡ ለክብርህ ፡ ታቆማለህ
ታሪኬ ፡ ታድሶልኝ ፡ ይኸው ፡ እዘምራለሁ

አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ መታሰቢያዬ ፡ የሱስዬ ፡ መታወቂያዬ ፡ ኢየሱስዬ (፬x)
መጀመሪያዬ ፡ ኢየሱስዬ ፡ መደምደሚያዬ ፡ ኢየሱስዬ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ

ጠላት ፡ ዙሪያዬን ፡ ሲዞር ፡ እያገሳ ፡ እንደ ፡ አንበሳ
ሊውጠኝም ፡ ሲከጅል ፡ መከራዬን ፡ ሲያበዛ
አንተ ፡ ተስፋዬ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ሁሉም ፡ በከፋ ፡ ጊዜ
ሌላ ፡ ረዳት ፡ የለኝም ፡ ረዳቴ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስዬ

አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጊዜ ፡ ታዳጊዬ ፡ ኢየሱስዬ ፡ ጠባቂዬ ፡ ኢየሱስዬ (፬x)
ማምለጫዬ ፡ ኢየሱስዬ ፡ መሸሸጊያዬ ፡ ኢየሱስዬ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ

ምንም ፡ ነገር ፡ በሌለበት ፡ ምድረበዳ ፡ ላይ
ዓይኖቼን ፡ በመታመን ፡ አንስቼ ፡ ወደላይ
ስጠራህ ፡ የማትዘገይ ፡ ፈጥነህ ፡ የምትደርስልኝ
ለችግር ፡ ለጭንቀቴ ፡ መፍትሔ ፡ የምትሆንልኝ

አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ (፬x)
መታመኛዬ ፡ ኢየሱስዬ ፡ መጽናኛዬ ፡ ኢየሱስዬ
መመኪያዬ ፡ ኢየሱስዬ ፡ መኖሪያዬ ፡ ኢየሱስዬ ፡ አንተኮ ፡ ነህ